ዘኍል 8:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም ሌዋውያን እግዚአብሔርን ያገለግሉ ዘንድ ከእስራኤል ልጆች መካከል ስጦታ አድርጎ፥ ሌዋውያንን በእግዚአብሔር ፊት ይለያቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አሮን ሌዋውያኑን የእግዚአብሔርን አገልግሎት ለማከናወን ዝግጁ እንዲሆኑ ከእስራኤላውያን መካከል እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ያቅርባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንም ሌዋውያን ጌታን እንዲያገለግሉ ከእስራኤል ልጆች መካከል ለመወዝወዝ ቁርባን ሌዋውያንን በጌታ ፊት ያቅርብ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዋውያን ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ለእኔ ለእግዚአብሔር እንደ ልዩ ስጦታ ሆነው በመቅረብ ያገለግሉኝ ዘንድ አሮን ይቀድሳቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም ሌዋውያን እግዚአብሔርን ያገለግሉ ዘንድ ከእስራኤል ልጆች መካከል ስጦታ አድርጎ፥ ሌዋውያንን በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ። |
የእርሱ እጆች ለእግዚአብሔር የእሳቱን ቍርባን ያመጣሉ፤ ፍርምባውን በእግዚአብሔር ፊት ቍርባን ያቀርብ ዘንድ በጉበቱ ላይ ያለውን መረብና የፍርምባውን ስብ ያመጣል።
ፍርምባውንና የቀኝ ወርቹን ከእስራኤል ልጆች ከደኅንነት መሥዋዕታቸው ወስጄአለሁ፤ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘለዓለም ሕግ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ሰጥቼአቸዋለሁ።”
ሙሴም ከቅድስናው አውራ በግ ፍርምባውን ወስዶ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበው ዘንድ ቈራረጠ። እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ይህ ለቅድስና ከታረደው አውራ በግ የሙሴ እድል ፈንታ ሆነ።
ካህኑም እነዚህን ሁሉ ቍርባን አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባል፤ ይህም የቍርባን ፍርምባና የመባው ወርች ለካህኑ የተቀደሰ ነው፤ ከዚያም በኋላ ባለስእለቱ ወይን ይጠጣል።
በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ይሸከም ዘንድ፥ እርሱንም ለማገልገል በእግዚአብሔር ፊት ይቆም ዘንድ፥ በስሙም ይባርክ ዘንድ እግዚአብሔር እስከ ዛሬ ድረስ የሌዊን ነገድ ለየ።