ዘኍል 7:89 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ወደ ምስክሩ ድንኳን እርሱን ለመነጋገር በገባ ጊዜ በቃል ኪዳኑ ታቦት ላይ ካለው ከስርየት መክደኛው በላይ ከኪሩቤልም መካከል የእግዚአብሔርን ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ከእርሱም ጋር ይናገር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋራ ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ ከምስክሩ ታቦት መክደኛ በላይ በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ድምፅ ሲናገረው ሰማ፤ አነጋገረውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ከጌታ ጋር ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ በምስክሩ ታቦት ላይ ካለው ከስርየት መክደኛ በላይ ከኪሩቤልም መካከል ድምፁ ሲናገረው ይሰማ ነበር፤ እንዲህም እርሱ ተናገረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በኪሩቤል መካከል ካለው ከቃል ኪዳኑ ታቦት መክደኛ በላይ ሆኖ ሲናገረው ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ወደ መገናኛው ድንኳን እርሱን ለመነጋገር በገባ ጊዜ በምስክሩ ታቦት ላይ ካለው ከስርየት መክደኛ በላይ ከኪሩቤልም መካከል ድምፁ ሲናገረው ይሰማ ነበር፤ እርሱም ይናገረው ነበር። |
ደመናውም በላዩ ስለነበር ድንኳኑም የእግዚአብሔርን ክብር ስለ ተሞላ ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ይገባ ዘንድ አልቻለም።
እግዚአብሔርም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ በምስክሩ ድንኳን ውስጥ፥ በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን፥ ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ዓመት እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
እኔም እወርዳለሁ፤ በዚያም አነጋግርሃለሁ፤ በአንተ ካለውም መንፈስ ወስጄ በእነርሱ ላይ አደርገዋለሁ፤ አንተም ብቻ እንዳትሸከም የሕዝቡን ሸክም ከአንተ ጋር ይሸከማሉ።
እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ እናገረዋለሁ፤ በስውርም አይደለም፤ የእግዚአብሔርንም ክብር ያያል፤ አገልጋዬ ሙሴን ማማትን ስለ ምን አልፈራችሁም?” አለ።
እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል፥ በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።
ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።
ሕዝቡም ወደ ሴሎ ላኩ፤ በኪሩቤልም ላይ የሚቀመጠውን የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከዚያ አመጡ፤ ሁለቱም የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።