ቍጥራቸውም ይህ ነው፤ ሠላሳ የወርቅ ሳሕኖች፥ አንድ ሺህም የብር ሳሕኖች፥ ሃያ ዘጠኝም ቢላዋዎች፥ ሠላሳ የወርቅ ዳካዎች፥
ዘኍል 7:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመባውም ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉትን፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነውን አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነውን አንድ የብር ድስት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመባውም ለእህል ቁርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉትን፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነውን አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነውን አንድ ጐድጓዳ ሳሕን አቀረበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለመባውም ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉትን፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነውን አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነውን አንድ የብር ድስት፤ |
ቍጥራቸውም ይህ ነው፤ ሠላሳ የወርቅ ሳሕኖች፥ አንድ ሺህም የብር ሳሕኖች፥ ሃያ ዘጠኝም ቢላዋዎች፥ ሠላሳ የወርቅ ዳካዎች፥
ለማፍሰሻም ይሆኑ ዘንድ ወጭቶችዋን፥ ጭልፋዎችዋንም፥ መቅጃዎችዋንም፥ ጽዋዎችዋንም አድርግ፤ እነርሱንም ከጥሩ ወርቅ አድርጋቸው።
ምንቸቶቹንና መጫሪያዎችን፥ መኰስተሪያዎችንና ድስቶችን፥ ጭልፋዎችንም፥ የሚያገለግሉበትንም የናስ ዕቃ ሁሉ ወሰዱ።
“ማናቸውም ሰው ቍርባን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲሆን ቢያቀርብ፥ ቍርባኑ ከመልካም ስንዴ ዱቄት ይሁን፤ ዘይትም ያፈስስበታል፤ ነጭ ዕጣንም ይጨምርበታል፤ ይህም መሥዋዕት ነው።
“ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ለማምጣት ገንዘብ በእጁ ባይኖረው፥ ስለ ሠራው ኀጢአት የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ ክፍል መልካም የስንዴ ዱቄት ለኀጢአት መሥዋዕት ያቀርባል፤ የኀጢአት መሥዋዕት ነውና ዘይት አያፈስስበትም፤ ዕጣንም አይጨምርበትም።
በዚያ ቀን በፈረሶች ሻኵራ ላይ፦ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ተብሎ ይጻፋል፣ በእግዚአብሔርም ቤት ያሉ ምንቸቶች በመሠዊያው ፊት እንዳሉ ዳካዎች ይሆናሉ።