ዘኍል 36:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች መሐላ፥ ቴርሳ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ኑኃ ከአባታቸው ወንድሞች ልጆች ጋር ተጋቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰለጰዓድ ሴት ልጆች፤ ማህለህ፣ ቲርጻ፣ ዔግላ፣ ሚልካ፣ ኑዓ ከአባታቸው ወንድሞች ልጆች ጋራ ተጋቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰለጰዓድ ልጆች ማህለህ፥ ቲርጻ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ኑዓ ከአባታቸው ወንድሞች ልጆች ጋር ተጋቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች ማሕላ፥ ቲርጻ፥ ሖግላ፥ ሚልካ እና ኖዓ ከአባታቸው ወንድሞች ልጆች ጋር ተጋቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰለጰዓድ ልጆች ማህለህ፥ ቲርጻ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ኑዓ ከአባታቸው ወንድሞች ልጆች ጋር ተጋቡ። |
ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ወገን ፥ የምናሴ ልጅ፥ የማኪር ልጅ፥ የገለአድ ልጅ፥ የኦፌር ልጅ፥ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች መጡ፤ የእነዚህም ሴቶች ልጆች ስሞች መሐላ፥ ኑኃ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበሩ።