ዓሣ አጥማጆችም ከዓይንጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይንኤግላይም ድረስ በዚያ ይቆማሉ። ያም መረብ መዘርጊያ ይሆናል፤ ዓሣዎችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣዎች በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።
ዘኍል 34:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለባሕርም ዳርቻ ታላቁ ባሕር ዳርቻችሁ ይሆናል፤ ይህ የባሕር ዳርቻችሁ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምዕራቡ ድንበራችሁ ደግሞ የታላቁ ባሕር ዳርቻ ይሆናል። በምዕራቡ በኩል ያለው ወሰናችሁም ይኸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለምዕራብም ድንበር ታላቁ ባሕርና ዳርቻው ድንበራችሁ ይሆናል፤ ይህ የምዕራብ ድንበራችሁ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የምዕራቡ ወሰን የሜድትራኒያን ባሕር ጠረፍ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለምዕራብም ዳርቻ ታላቁ ባሕር ዳርቻችሁ ይሆናል፤ ይህ የምዕራብ ዳርቻችሁ ይሆናል። |
ዓሣ አጥማጆችም ከዓይንጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይንኤግላይም ድረስ በዚያ ይቆማሉ። ያም መረብ መዘርጊያ ይሆናል፤ ዓሣዎችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣዎች በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።
የምዕራቡም ድንበር ከደቡቡ ድንበር ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ አንጻር ድረስ ታላቁ ባሕር ይሆናል። የምዕራቡ ድንበር ይህ ነው።
ከሊባኖስ ፊት ለፊት ምድረ በዳ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ የኬጤዎናውያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ወሰናችሁ ይሆናል።
ድንበሩም ወደ አቃሮን ደቡብ ይወጣል፤ ወደ ሰሜን ወገን ይመለሳል፤ ድንበሩ ወደ ሰቆት ይወጣል፤ ወደ ደቡብም ያልፋል፤ በሌብና በኩልም ይወጣል፤ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ።
በባሕር በኩል ያለው ድንበራቸውም እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ። ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው።
አሴያዶት መንደሮችዋና መሰማሪያዎችዋም፥ ጋዛም መንደሮችዋና መሰማሪያዎችዋም እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ፥ ታላቁ ባሕርም ወሰኑ ነው።
እነሆ እኔ ካጠፋኋቸው አሕዛብ ሁሉ ጋር ከዮርዳኖስ ጀምሮ በፀሐይ መግቢያ እስካለው እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ለነገዶቻችሁ ርስት እንዲሆኑ የቀሩትን እነዚህን አሕዛብ በዕጣ ከፈልሁላችሁ።
እንዲህም ሆነ፤ በዮርዳኖስ ማዶ በተራራማው በሜዳውም በታላቁ ባሕር ዳር በሊባኖስም ፊት ለፊት የነበሩ ነገሥት ሁሉ፥ ኬጤዎናዊዉ፥ አሞሬዎናዊዉም፥ ከነዓናዊዉም፥ ፌርዜዎናዊዉም፥ ኤዌዎናዊዉም፥ ኢያቡሴዎናዊዉም፥ ጌርጌሴዎናዊዉም ይህን በሰሙ ጊዜ፥