Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 34:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ለምዕራብም ዳርቻ ታላቁ ባሕር ዳርቻችሁ ይሆናል፤ ይህ የምዕራብ ዳርቻችሁ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የምዕራቡ ድንበራችሁ ደግሞ የታላቁ ባሕር ዳርቻ ይሆናል። በምዕራቡ በኩል ያለው ወሰናችሁም ይኸው ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “ለምዕራብም ድንበር ታላቁ ባሕርና ዳርቻው ድንበራችሁ ይሆናል፤ ይህ የምዕራብ ድንበራችሁ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “የምዕራቡ ወሰን የሜድትራኒያን ባሕር ጠረፍ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “ለባ​ሕ​ርም ዳርቻ ታላቁ ባሕር ዳር​ቻ​ችሁ ይሆ​ናል፤ ይህ የባ​ሕር ዳር​ቻ​ችሁ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 34:6
12 Referencias Cruzadas  

አጥማጆችም በዚያ ይቆማሉ፥ ከዓይንጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይንኤግላይም ድረስ መረብ መዘርጊያ ይሆናል፥ ዓሣዎችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣዎች በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።


የምድሪቱም ድንበር ይህ ነው። በሰሜኑ ወገን ከታላቁ ባሕር ጀምሮ በሔትሎን መንገድ ወደ ጽዳድ መግቢያ፥


የምዕራቡም ድንበር ከደቡቡ ድንበር ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ አንጻር ድረስ ታላቁ ባሕር ይሆናል። የምዕራቡ ድንበር ይህ ነው።


ዳርቻውም ከዓጽሞን ወደ ግብፅ ወንዝ ይዞራል፥ መውጫውም በባሕሩ በኩል ይሆናል።


የሰሜንም ዳርቻችሁ ይህ ይሆናል፤ ከታላቁ ባሕር ወደ ሖር ተራራ ምልክት ታመለክታላችሁ።


የንፍታሌምንም ምድር ሁሉ፥ የኤፍሬምንና የምናሴንም ምድር፥ እስከ ምዕራብም ባሕር ድረስ ያለውን የይሁዳን ምድር ሁሉ፥ ደቡቡንም፥


ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ የኬጥያውያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግቢያ እስክ ታላቁ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል።


ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፥ ወደ ሽክሮን ደረሰ፥ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤል በኩልም ወጣ፥ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ።


በምዕራብም በኩል ያለው ድንበር እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ። ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው።


አዛጦንና የተመሸጉና ያልተመሸጉ መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ያልተመሸጉም መንደሮችዋ፥ እስከ ግብፅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ዳርቻ ድረስ።


እነሆ፥ እኔ ካጠፋኋቸው አሕዛብ ሁሉ ጋር ከዮርዳኖስ ጀምሮ በፀሐይ መግቢያ እስካለው እስከ ታልቁ ባሕር ድረስ ለነገዶቻችሁ ርስት እንዲሆኑ የቀሩትን እነዚህን አሕዛብ በዕጣ ከፈልሁላችሁ።


እንዲህም ሆነ፥ በዮርዳኖስ ማዶ በተራራማው በቈላማውም በታላቁ ባሕር ዳር በሊባኖስም ፊት ለፊት የነበሩ ነገሥታት ሁሉ፥ ኬጢያዊ አሞራዊም ከነዓናዊም ፌርዛዊም ኤዊያዊም ኢያቡሳዊም፥ ይህን በሰሙ ጊዜ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos