በዚያችም ቀን እግዚአብሔር ለአብራም ተስፋ ያደረገለትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እንዲህም አለው፥ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣታለሁ፤
ዘኍል 34:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፥ “እግዚአብሔር ለዘጠኙ ነገድና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ይሰጡአቸው ዘንድ እንደ አዘዘ በዕጣ የምትወርሱአት ምድር ይህች ናት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤ “ይህችን ምድር ርስት አድርጋችሁ በዕጣ ደልድሉ፤ እግዚአብሔርም ለዘጠኙና ለግማሹ ነገድ እንድትሰጥ አዝዟል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ጌታ ለዘጠኝ ነገድ ተኩል እንዲሰጥ ያዘዘው በዕጣ የምትወርሱአት ምድር ይህች ናት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ለዘጠኝ ተኩል ነገዶች እንዲሰጥ እግዚአብሔር ያዘዘው በዕጣ የምትካፈሉት ርስት ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ እግዚአብሔር ለዘጠኝ ነገድ ተኩል ይሰጡአቸው ዘንድ ያዘዘ በዕጣ የምትወርሱአት ምድር ይህች ናት፤ |
በዚያችም ቀን እግዚአብሔር ለአብራም ተስፋ ያደረገለትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እንዲህም አለው፥ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣታለሁ፤
“ርስትም አድርጋችሁ ምድርን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ከምድር የተቀደሰውን የዕጣ ክፍል መባ አድርጋችሁ ወደ እግዚአብሔር ታቀርባላችሁ። ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ፥ ወርዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆናል፤ በዳርቻው ሁሉ ዙሪያው የተቀደሰ ይሆናል።
የእግራችሁ ጫማ የምትረግጣት ስፍራ ሁሉ ለእናንተ ትሆናለች፤ ከምድረ በዳም፥ ከአንጢሊባኖስም፥ ከታላቁም ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል።
አሁንም ይህን ምድር ለዘጠኙ ነገድ፥ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገህ ክፈለው። ከዮርዳኖስ ጀምሮ በምዕራብ እስካለው ታላቁ ባሕር ድረስ ትሰጣቸዋለህ፤ ድንበራቸውም ታላቁ ባሕር ይሆናል።”