Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 34:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ዳር​ቻ​ውም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ይወ​ር​ዳል፤ መው​ጫ​ውም በጨው ባሕር ይሆ​ናል። ምድ​ራ​ችሁ እንደ ዳር​ቻዋ በዙ​ሪ​ያዋ ይህች ናት።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከዚያም ወሰኑ የዮርዳኖስን ወንዝ ተከትሎ መጨረሻው የጨው ባሕር ይሆናል። “ ‘እንግዲህ በዙሪያዋ ካሉት ወሰኖቿ ጋራ ምድራችሁ ይህች ናት።’ ”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ድንበሩም ወደ ዮርዳኖስ ይወርዳል፥ መጨረሻውም በጨው ባሕር ይሆናል። ምድራችሁ እንደ ድንበርዋ በዙሪያዋ ይህች ናት።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ወሰኑም ወደ ዮርዳኖስ ይወርዳል፤ መጨረሻውም የሙት ባሕር ይሆናል። እነዚህም የምድራችሁ ዙሪያ አዋሳኞች ይሆናሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ዳርቻውም ወደ ዮርዳኖስ ይወርዳል፥ መውጫውም በጨው ባሕር ይሆናል። ምድራችሁ እንደ ዳርቻዋ በዙሪያዋ ይህች ናት።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 34:12
10 Referencias Cruzadas  

የአ​ዜቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ በኤ​ዶ​ም​ያስ መያ​ያዣ ይሆ​ናል፤ የአ​ዜ​ብም ዳርቻ ከጨው ባሕር ዳር በም​ሥ​ራቅ በኩል ይጀ​ም​ራል፤


እነ​ዚህ ሁሉ በኤ​ሌ​ቄን ሸለቆ ተሰ​ብ​ስ​በው ተባ​በሩ፤ ይኸ​ውም የጨው ባሕር ነው።


ሎጥም ዓይ​ኖ​ቹን አነሣ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዙሪያ ያለ​ው​ንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞ​ላ​በት መሆ​ኑን አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን ከማ​ጥ​ፋቱ አስ​ቀ​ድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነ​ትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።


ዳር​ቻ​ውም ከሴ​ፋማ በዐ​ይን ምሥ​ራቅ ወዳ​ለው ወደ አር​ቤላ ይወ​ር​ዳል፤ እስከ ኬኔ​ሬት የባ​ሕር ወሽ​መጥ በም​ሥ​ራቅ በኩል ይደ​ር​ሳል፤


ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ጠኙ ነገ​ድና ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ይሰ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ እንደ አዘዘ በዕጣ የም​ት​ወ​ር​ሱ​አት ምድር ይህች ናት፤


ድን​በ​ር​ህ​ንም ከኤ​ር​ትራ ባሕር እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ባሕር፥ ከም​ድረ በዳም እስከ ታላቁ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ አሰ​ፋ​ለሁ፤ በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን በእ​ጅህ እጥ​ላ​ለ​ሁና፤ ከአ​ን​ተም አስ​ወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ኢያ​ሱም ሸመ​ገለ፤ ዘመ​ኑም አለፈ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን አለው፥ “እነሆ ዘመ​ንህ አለፈ፤ ያል​ተ​ወ​ረ​ሰች እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀር​ታ​ለች፤


በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸው እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮር​ዳ​ኖ​ስም ነበረ። በሰ​ሜ​ንም በኩል ያለው ድን​በር በዮ​ር​ዳ​ኖስ መጨ​ረሻ እስ​ካ​ለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበረ፤


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ ለዐ​ሥራ ሁለቱ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ምድ​ሪ​ቱን የም​ት​ከ​ፍ​ሉ​በት ድን​በር ይህ ነው። ለዮ​ሴፍ ሁለት ዕጣ ይሆ​ናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios