“ተመልሰው በመግደሎና በባሕር መካከል፥ በብኤልሴፎን ፊት ለፊት ባለው ገላጣ መንደር አንጻር እንዲሰፍሩ ለእስራኤል ልጆች ተናገር፤ ከእርሱም አጠገብ በባሕር ዳር ትሰፍራላችሁ።
ዘኍል 33:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኤሮትም ፊት ለፊት ተጕዘው በባሕሩ መካከል ወደ ምድረ በዳ ተሻገሩ፤ በኤታምም በረሃ የሦስት ቀን መንገድ ሄደው በምረት ሰፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፊሃሒሮት ተነሥተው በባሕሩ ውስጥ በማለፍ ወደ ምድረ በዳው ሄዱ፤ ከዚያም በኤታም ምድረ በዳ ሦስት ቀን ተጕዘው በማራ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፊሀሒሮትም ተጉዘው ባሕሩን በመሻገር ወደ ምድረ በዳ አለፉ፤ በኤታምም በረሀ የሦስት ቀን መንገድ ሄደው በማራ ሰፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፒሃሒሮት ተነሥተው ቀይ ባሕርን በመሻገር ወደ ሱር በረሓ መጡ፤ ከሦስት ቀን ጒዞ በኋላ በማራ ሰፈሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፊሀሒሮትም ተጕዘው በባሕሩ ውስጥ ወደ ምድረ በዳ አለፉ፤ በኤታምም በረሀ የሦስት ቀን መንገድ ሄደው በማራ ሰፈሩ። |
“ተመልሰው በመግደሎና በባሕር መካከል፥ በብኤልሴፎን ፊት ለፊት ባለው ገላጣ መንደር አንጻር እንዲሰፍሩ ለእስራኤል ልጆች ተናገር፤ ከእርሱም አጠገብ በባሕር ዳር ትሰፍራላችሁ።