ዘኍል 33:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም በሖር ተራራ ላይ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሃያ ሦስት ዓመት ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮን በሖር ተራራ ላይ ሲሞት፣ ዕድሜው መቶ ሃያ ሦስት ዓመት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንም በሖር ተራራ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ሦስት ዓመት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮንም በሖር ተራራ በሞተ ጊዜ ዕድሜው 123 ዓመት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም በሖር ተራራ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ሦስት ዓመት ነበር። |
ካህኑም አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፤ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት፥ በአምስተኛው ወር፥ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።