ኢዮሳፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ይወስዱ ዘንድ መጡ፤ ብዙ ከብትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብስም፥ እጅግም ያማረ ዕቃ አገኙ፤ ማረኩትም፤ ምርኮውም ብዙ ነበርና ምርኮውን እየሰበሰቡ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቈዩ።
ዘኍል 31:53 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ሁሉ የማረኩትን ለየራሳቸው ወሰዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱም ወታደር ለራሱ የወሰደው ምርኮ ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወታደሮቹም ሁሉ ከምርኮአቸው ለራሳቸው ወሰዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጦር ሹማምንት ያልሆኑት ወታደሮች ግን ያመጡትን ምርኮ ለራሳቸው አስቀሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ሁሉ ከምርኮአቸው ለራሳቸው ወሰዱ። |
ኢዮሳፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ይወስዱ ዘንድ መጡ፤ ብዙ ከብትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብስም፥ እጅግም ያማረ ዕቃ አገኙ፤ ማረኩትም፤ ምርኮውም ብዙ ነበርና ምርኮውን እየሰበሰቡ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቈዩ።
ከሻለቆችና ከመቶ አለቆች ለእግዚአብሔር የለዩትና ያቀረቡት ወርቅ ሁሉ ዐሥራ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ አምሳ ሰቅል ነበረ።
የምድያምንም ሴቶችና ልጆቻቸውን ማረኩ፤ እንስሶቻቸውንና ዕቃቸውን፥ ንብረታቸውንና ኀይላቸውን በዘበዙ።
ከሴቶቹና ከጓዙ በቀር እንስሶቹን፥ በከተማዪቱም ያለውን ምርኮ ሁሉ ዘርፈህ ለአንተ ትወስዳለህ፤ አምላክህም እግዚአብሔር የሚሰጥህን የጠላቶችህን ምርኮ ትበላለህ።