ከእናንተም አምስቱ መቶውን ያሳድዳሉ፤ መቶውም ዐሥሩን ሺህ ያሳድዳሉ፤ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።
ዘኍል 31:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦርነት ስደዱ፤” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ አንዳንድ ሺሕ ሰው ለጦርነቱ ላኩ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከየነገዱ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦርነት ላኩ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንዳንድ ሺህ ወንዶችን መርጣችሁ ወደ ጦርነቱ ላኩ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከየነገዱ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦርነት ስደዱ ብሎ ተናገራቸው። |
ከእናንተም አምስቱ መቶውን ያሳድዳሉ፤ መቶውም ዐሥሩን ሺህ ያሳድዳሉ፤ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።
ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ ብሎ ነገራቸው፥ “ከእናንተ መካከል ሰዎችን አስታጥቁ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምድያምን ይበቀሉ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ከምድያም ጋር ይሰለፉ።
እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፥ “ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፤ ስለዚህ እስራኤል፦ እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም።”
ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፥ ወደ እነዚህ ቈላፋን ሰፈር እንለፍ፤ በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና ምናልባት እግዚአብሔር ይረዳን ይሆናል” አለው።