La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 31:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከድ​ር​ሻ​ቸው እኩ​ሌታ ወስ​ደህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቀዳ​ም​ያት ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህንም ግብር ከድርሻቸው ላይ ወስደህ የእግዚአብሔር ፈንታ በማድረግ ለካህኑ ለአልዓዛር ስጠው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከድርሻቸው ወስደህ ለጌታ እንደ ስጦታ ቁርባን አግርህ ለካህኑ ለአልዓዛር ትሰጠዋለህ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለእኔ ለእግዚአብሔር ልዩ ስጦታ በማድረግም ለካህኑ ለአልዓዛር ስጡት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከድርሻቸው ወስደህ ለእግዚአብሔር ለማንሣት ቍርባን ለካህኑ ለአልዓዛር ስጠው።

Ver Capítulo



ዘኍል 31:29
7 Referencias Cruzadas  

ከሚ​ካ​ኑ​በ​ትም አውራ በግ የተ​ወ​ሰደ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ወግ የሚ​ሆን ለመ​ሥ​ዋ​ዕት የተ​ለ​የ​ውን ፍር​ም​ባና የተ​ነ​ሣ​ውን ወርች ትቀ​ድ​ሳ​ለህ።


“ለሌ​ዋ​ው​ያን እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእ​ና​ንተ ርስት አድ​ርጌ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁን ዐሥ​ራት በተ​ቀ​በ​ላ​ችሁ ጊዜ፥ እና​ን​ተ​ም​ከ​እ​ርሱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አድ​ር​ጋ​ችሁ የዐ​ሥ​ራት ዐሥ​ራት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።


እን​ዲሁ እና​ንተ ደግሞ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከም​ት​ቀ​በ​ሉት ዐሥ​ራት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አድ​ር​ጋ​ችሁ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መባ ለይ​ታ​ችሁ ለካ​ህኑ ለአ​ሮን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።


ከእ​ነ​ዚ​ያም ከተ​ዋ​ጉት፥ ወደ ሰል​ፍም ከወ​ጡት ሰል​ፈ​ኞች ዘንድ ከሰ​ዎ​ችም፥ ከበ​ሬ​ዎ​ችም፥ ከበ​ጎ​ችም፥ ከአ​ህ​ዮ​ችም፥ ከአ​ም​ስት መቶ አንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግብር ታወ​ጣ​ላ​ችሁ።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ድርሻ እኩ​ሌታ፥ ከሰ​ዎ​ችም፥ ከበ​ሬ​ዎ​ችም፥ ከበ​ጎ​ችም፥ ከአ​ህ​ዮ​ችም፥ ከእ​ን​ስ​ሶ​ችም ሁሉ ከአ​ምሳ አንድ ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ድን​ኳን ሥር​ዐት ለሚ​ጠ​ብቁ ለሌ​ዋ​ው​ያን ትሰ​ጣ​ለህ።”


እና​ን​ተም፥ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ች​ሁም፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ክፍ​ልና ርስት ስለ​ሌ​ለው በደ​ጆ​ቻ​ችሁ ውስጥ የተ​ቀ​መ​ጠው ሌዋ​ዊም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


በም​ድ​ርህ ላይ በም​ት​ኖ​ር​በት ዘመን ሁሉ ሌዋ​ዊ​ዉን ቸል እን​ዳ​ትል ተጠ​ን​ቀቅ።