ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ እጅግ ብዙ ደም አፍስሰሃል፤ ታላቅም ሰልፍ አድርገሃል፤ በፊቴም በምድር ላይ ብዙ ደም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም።
ዘኍል 31:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም ከሰፈሩ ውጭ ሰባት ቀን ስፈሩ፤ ሰውን የገደለ ሁሉ፥ የተገደለውንም የዳሰሰ ሁሉ፥ እናንተና የማረካችኋቸውም በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሰውነታችሁን ንጹሕ አድርጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከእናንተ መካከል ሰው የገደለ ወይም የተገደለውን የነካ ሁሉ ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን ይቈይ። በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሳችሁንና ምርኮኞቻችሁን አንጹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰፈሩም ውጭ ሰባት ቀን ስፈሩ፤ ከእናንተም ሰውን የገደለ ሁሉ የተገደለውንም የነካ ሁሉ፥ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሳችሁንና እናንተ የማረካችኋቸውን አንጹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናንተ መካከል ሰው የገደለ ወይም ሬሳ የነካ ሁሉ ለሰባት ቀን ከሰፈር ውጪ ይቈይ፤ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሳችሁንና የማረካችኋቸውን ሴቶች አንጹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰፈሩም ውጭ ሰባት ቀን ስፈሩ፤ ሰውን የገደለ ሁሉ የተገደለውንም የዳሰሰ ሁሉ፥ እናንተ የማረካችኋቸውም በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሰውነታችሁን ንጹሕ አድርጉ። |
ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ እጅግ ብዙ ደም አፍስሰሃል፤ ታላቅም ሰልፍ አድርገሃል፤ በፊቴም በምድር ላይ ብዙ ደም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም።
“የእስራኤል ልጆች ለምጻሙን ሁሉ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ በሰውነቱ የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ እዘዛቸው፤