ለሴቲቱም እግዚአብሔር አላት፥ “ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ከወለድሽም በኋላ ፈቃድሽ ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም ይገዛሻል።”
ዘኍል 30:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባልዋም ቢሰማ፥ በሰማበትም ቀን ዝም ቢላት፥ ስእለቷ፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ይጸናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሏም ሰምቶ ምንም ነገር ሳይላት ቢቀር ስእለቶቿ ወይም ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችባቸው ነገሮች መፈጸም ይኖርባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባልዋም ቢሰማ፥ በሰማበትም ቀን ዝም ቢላት፥ ስእለትዋ ይጸናል፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ይጸናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባልዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ካልከለከላት በቀር ስእለትዋንም ሆነ የገባችውን ቃል መፈጸም አለባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባልዋም ቢሰማ፥ በሰማበትም ቀን ዝም ቢላት፥ ስእለትዋ ይጸናል፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ይጸናል። |
ለሴቲቱም እግዚአብሔር አላት፥ “ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ከወለድሽም በኋላ ፈቃድሽ ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም ይገዛሻል።”
እኛስ ለሰማይ ንግሥት ባጠንንላት፥ የመጠጥንም ቍርባን ባፈሰስንላት ጊዜ፥ በውኑ ያለ ባሎቻችን ምስልዋን ለማበጀት እንጎቻ አድርገንላት ኖሮአልን? የመጠጥንም ቍርባን አፍስሰንላት ኖሮአልን?”
ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለቷና ራስዋን ያሰረችበት መሐላ አይጸኑም፤ ባልዋ ከልክሎአታልና፤ እግዚአብሔርም ይቅር ይላታል።
ባል ያላት ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ ከእርሱ ጋር በሕግ የታሰረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን በሚስትነት ታስራበት ከኖረችው ሕግ የተፈታች ናት።
እርስዋም፥ “አዶናይ፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የባርያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለአንተ እሰጠዋለሁ፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥም አይጠጣም። ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም” ብላ ስእለት ተሳለች።
ባልዋም ሕልቃና፥ “በዐይንሽ ደስ ያሰኘሽን አድርጊ፤ ጡትም እስኪተው ድረስ ተቀመጪ፤ ብቻ እግዚአብሔር ከአፍሽ የወጣውን ያጽና” አላት። ሴቲቱም ልጅዋን እያጠባች ጡት እስኪተው ድረስ ተቀመጠች።