ዘኍል 3:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሜራሪም ልጆች በየወገናቸው፤ ሞሐሊ፥ ሙሲ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሜራሪ ጐሣዎች፤ ሞሖሊና ሙሲ። እንግዲህ የሌዋውያን ጐሣዎች በየቤተ ሰባቸው ሲቈጠሩ እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሜራሪም ልጆች በየወገኖቻቸው፤ ሞሖሊ፥ ሙሲ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሜራሪ ወንዶች ልጆች ማሕሊናና ሙሺ ይባሉ ነበር፤ እነዚህም በየስማቸው የቤተሰብ አባቶች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሜራሪም ልጆች በየወገናቸው፤ ሞሖሊ፥ ሙሲ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው። |
ከኤዶትም የኤዶትም ልጆች፤ ጎዶልያስ፥ ሱሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸብያ፥ መታትያ፥ እነዚህ ስድስቱ ከአባታቸው ከኤዶትም ጋር በበገና እየዘመሩ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።
ሌዋውያኑም፥ ከቀዓት ልጆች የአሜሳእ ልጅ መኤትና የዓዛርያስ ልጅ ኢዮሔል፥ ከሜራሪም ልጆች የአብዲ ልጅ ቂስና የያሃሌልኤል ልጅ ዓዛርያስ፥ ከጌድሶንም ልጆች የዛማት ልጅ ዮአክና የዮአክ ልጅ ኢዮአድ፤
በየአባቶቻቸውም ቤት ለተቈጠሩ ካህናት፥ ከሃያ ዓመትም ወደ ላይ ላሉ በየሥርዐታቸውና በየሰሞናቸው ለተቈጠሩ ሌዋውያን፥
እነዚህም እንደ ወገኖቻቸው የሌዊ ልጆች ስሞች ናቸው፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌዊም የሕይወት ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።