ዘኍል 3:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀዓትም ልጆች በየወገናቸው እንበረም፥ ይሳዓር፥ ኬብሮን፥ አዛሄል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀዓት ጐሣዎች፤ እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀዓትም ልጆች በየወገኖቻቸው፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀዓትም ወንዶች ልጆች ዓምራም፥ ይጽሐር፥ ኬብሮንና ዑዚኤል ይባሉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀዓትም ልጆች በየወገናቸው፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል። |
ከኤማን የኤማን ልጆች፤ ቡቅያ፥ መታንያ፥ ዓዛርዔል፥ ሱባኤል፥ ኢየሪሙት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤልያታ፥ ጌዶላቲ፥ ሮማንቴዔዜር፥ ዮስብቃሳ፥ ሜኤላቴ፥ ሆቴር፥ መሐዝዮት፤
ሌዋውያኑም፥ ከቀዓት ልጆች የአሜሳእ ልጅ መኤትና የዓዛርያስ ልጅ ኢዮሔል፥ ከሜራሪም ልጆች የአብዲ ልጅ ቂስና የያሃሌልኤል ልጅ ዓዛርያስ፥ ከጌድሶንም ልጆች የዛማት ልጅ ዮአክና የዮአክ ልጅ ኢዮአድ፤
እነዚህም እንደ ወገኖቻቸው የሌዊ ልጆች ስሞች ናቸው፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌዊም የሕይወት ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።
እንበረምም የአባቱን ወንድም ልጅ ዮካብድን አገባ፤ አሮንንና ሙሴን፥ እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት፤ የእንበረምም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።
ለቀዓትም የእንበረም ወገን፥ የይስዓር ወገን፥ የኬብሮንም ወገን፥ የአዛሔልም ወገን ነበሩ፤ የቀዓት ወገኖች እነዚህ ናቸው።