ዘኍል 28:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዐሥራ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ፋሲካ በዓል ይከበራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዓሥራ አራተኛው ቀን የጌታ ፋሲካ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የጌታ የፋሲካ በዓል የሚከበረው የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጀመሪያው ወር ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው። |
ከመጀመሪያውም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን ሠርክ ጀምራችሁ እስከዚሁ ወር ሃያ አንደኛ ቀን ሠርክ ድረስ ቂጣ ትበላላችሁ።
የቂጣውን በዓል ጠብቁ፤ በአዲስ ወር ከግብፅ ምድር ወጥታችኋልና በዚህ ወር እንዳዘዝኋችሁ ሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ።
“የቂጣውን በዓል ትጠብቀዋለህ። በሚያዝያ ወር ከግብፅ ወጥተሃልና በታዘዘው ዘመን በሚያዝያ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።