ለአንድም ወይፈን አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለአንድም አውራ በግ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለአንድም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ለእህል ቍርባን ያቅርብ።
ዘኍል 28:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእያንዳንዱም ወይፈን ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ መልካም ዱቄት፥ ለአውራው በግ ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ፥ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእያንዳንዱ ወይፈን ጋራ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ ልም ዱቄት፣ ከአውራውም በግ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት ይቀርባል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ደግሞ ለእያንዳንዱም ወይፈን ለእህል ቁርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ መልካም ዱቄት፥ ለአንድ አውራ በግም ለእህል ቁርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእህልም ቊርባን በወይራ ዘይት የተለወሰ ምርጥ ዱቄት አቅርቡ፤ ይኸውም ከእያንዳንዱ ኰርማ ጋር ሦስት ኪሎ ዱቄት፥ ከአውራው በግ ጋር ሁለት ኪሎ ዱቄት፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእያንዳንዱም ወይፈን ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሦስት እጅ መልካም ዱቄት፥ ለአውራው በግም ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥ |
ለአንድም ወይፈን አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለአንድም አውራ በግ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለአንድም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ለእህል ቍርባን ያቅርብ።
የአሮንም ልጆች ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ያቀርቡታል፤ የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ነው።
ለእያንዳንዱም ጠቦት ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ፥ ከመስፈሪያው ዐሥረኛ እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን በእሳት ታቀርባላችሁ።