La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 27:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እንደ አዘ​ዘው፥ እጁን በላዩ ጫነ​በ​ትና፥ ሾመው፤ አዘ​ዘ​ውም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘው መሠረት እጁን በራሱ ላይ ጭኖ ሾመው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም በሙሴ እንደ ተናገረ፥ እጁን በእርሱ ላይ ጫነበት፥ አዘዘውም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሙሴ እጆቹን በኢያሱ ራስ ላይ ጭኖ ከዚያ በኋላ የእርሱ ተተኪ መሆኑን በግልጥ አስታወቀ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም በሙሴ እንደ ተናገረ፥ እጁን በላዩ ጫነበት፥ አዘዘውም።

Ver Capítulo



ዘኍል 27:23
9 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ያለ​በ​ትን ሰው የነ​ዌን ልጅ ኢያ​ሱን ወስ​ደህ እጅ​ህን በላዩ ጫን​በት፤


በካ​ህ​ኑም በአ​ል​ዓ​ዛር ፊት አቁ​መው፤ በማ​ኅ​በ​ሩም ፊት እዘ​ዘው፤ ስለ እር​ሱም በፊ​ታ​ቸው እዘዝ።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ፤ ኢያ​ሱ​ንም ወስዶ በካ​ህኑ በአ​ል​ዓ​ዛ​ርና በማ​ኅ​በሩ ሁሉ ፊት አቆ​መው፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


በዚ​ያም ጊዜ ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብዬ አዘ​ዝ​ሁት፦ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ነ​ዚህ በሁ​ለቱ ነገ​ሥት ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ዐይ​ኖ​ችህ አይ​ተ​ዋል፤ እን​ዲሁ በም​ታ​ል​ፍ​ባ​ቸው መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ር​ጋል።


ኢያሱ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሻ​ገ​ራ​ልና፥ አን​ተም የም​ታ​ያ​ትን ምድር እርሱ ያወ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ልና ኢያ​ሱን እዘ​ዘው፤ አደ​ፋ​ፍ​ረ​ውም፥ አጽ​ና​ውም።


የነ​ዌ​ንም ልጅ ኢያ​ሱን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ታገ​ባ​ለ​ህና ጽና፤ በርታ፤ እር​ሱም ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል” ብሎ አዘ​ዘው።


ሙሴም እጆ​ቹን ስለ ጫነ​በት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥ​በ​ብን መን​ፈስ ተሞላ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ታዘ​ዙ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ።