እንበረምም የአባቱን ወንድም ልጅ ዮካብድን አገባ፤ አሮንንና ሙሴን፥ እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት፤ የእንበረምም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።
ዘኍል 26:58 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ የሌዊ ልጆች ወገኖች ናቸው፤ የሎቢኒ ወገን፥ የኬብሮን ወገን፥ የሞሓሊ ወገን፥ የሐሙሲ ወገን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህም ደግሞ የሌዊ ጐሣዎች ነበሩ፤ የሊብናውያን ጐሣ፣ የኬብሮናውያን ጐሣ፣ የሞሖላውያን ጐሣ፣ የሙሳውያን ጐሣ፣ የቆሬያውያን ጐሣ። ቀዓት የእንበረም አባት ነበረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ የሌዊ ወገኖች ናቸው፤ የሊብናውያን ወገን፥ የኬብሮናውያን ወገን፥ የሞሖላውያን ወገን፥ የሙሳውያን ወገን፥ የቆሬያውያን ወገን። ቀዓትም እንበረምን ወለደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነርሱ ዘሮች የሊብናውያን ወገን፥ የኬብሮናውያን ወገን፥ የሞላውያን ወገን፥ የሙሳውያን ወገን፥ የቆሬያውያን ወገን ቀዓትም አምራምን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ የሌዊ ወገኖች ናቸው፤ የሊብናውያን ወገን፥ የኬብሮናውያን ወገን፥ የሞሖላውያን ወገን፥ የሙሳውያን ወገን፥ የቆሬያውያን ወገን። ቀዓትም እንበረምን ወለደ። |
እንበረምም የአባቱን ወንድም ልጅ ዮካብድን አገባ፤ አሮንንና ሙሴን፥ እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት፤ የእንበረምም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።
የሌዊም ልጅ የቀዓት ልጅ የይስዓር ልጅ ቆሬ ከኤልያብ ልጆች ከዳታንና ከአቤሮን፥ ከሮቤልም ልጅ ከፋሌት ልጅ ከአውናን ጋር ተናገረ።
ለቀዓትም የእንበረም ወገን፥ የይስዓር ወገን፥ የኬብሮንም ወገን፥ የአዛሔልም ወገን ነበሩ፤ የቀዓት ወገኖች እነዚህ ናቸው።