ዘኍል 26:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንፍታሌም ልጆች በየወገናቸው፤ ከአሴሔል የአሴሔላውያን ወገን፥ ከጎሄኒ የጎሄናውያን ወገን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንፍታሌም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በያሕጽኤል በኩል፣ የያሕጽኤላውያን ጐሣ፣ በጉኒ በኩል፣ የጉናውያን ጐሣ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየወገናቸው የንፍታሌም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከያሕጽኤል የያሕጽኤላውያን ወገን፥ ከጉኒ የጉናውያን ወገን፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የንፍታሌም ነገድ ተወላጆች ያሕጼል፥ ጉኒ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የንፍታሌም ልጆች በየወገናቸው፤ ከያሕጽኤል የያሕጽኤላውያን ወገን፥ ከጉኒ የጉናውያን ወገን፥ |
የንፍታሌም ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደ እየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥