የብንያምም ልጆች፤ ቤላ፥ ቦኮር፥ አስቤር፤ የቤላ ልጆችም፤ ጌራ፥ ኖሔማን፥ አሒ፥ ሮስ፥ ማንፌን፥ ሑፈም፤ ጌራም አራድን ወለደ።
ዘኍል 26:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ የኤፍሬም ልጆች ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የዮሴፍ ልጆች እነዚህ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ የብንያም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ ዐምስት ሺሕ ስድስት መቶ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየወገናቸው የብንያም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የብንያም ነገድ ተወላጆች እነዚህ ናቸው። ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በየወገናቸው የብንያም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። |
የብንያምም ልጆች፤ ቤላ፥ ቦኮር፥ አስቤር፤ የቤላ ልጆችም፤ ጌራ፥ ኖሔማን፥ አሒ፥ ሮስ፥ ማንፌን፥ ሑፈም፤ ጌራም አራድን ወለደ።
የብንያም ልጆች በየወገናቸው፤ ከበዓሌ የበዓላውያን ወገን፥ ከአሲቤር የአሲቤራውያን ወገን፥ ከአኪራን የአኪራናውያን ወገን፥
በዚያም ቀን ከየከተማው የመጡ የብንያም ልጆች ተቈጠሩ፤ ቍጥራቸውም ከገባዖን ሰዎች ሌላ ሃያ አምስት ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከገባዖንም ሰባት መቶ የተመረጡ ሰዎች ተቈጠሩ፤