Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 20:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በዚ​ያም ቀን ከየ​ከ​ተ​ማው የመጡ የብ​ን​ያም ልጆች ተቈ​ጠሩ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ከገ​ባ​ዖን ሰዎች ሌላ ሃያ አም​ስት ሺህ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም ሰባት መቶ የተ​መ​ረጡ ሰዎች ተቈ​ጠሩ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ብንያማውያንም ከመላው የጊብዓ ነዋሪዎች መካከል ከተመረጡት ሰባት መቶ ሰዎች ሌላ፣ ሰይፍ የታጠቁ ሃያ ስድስት ሺሕ ሰዎች በአንድ አፍታ ከየከተሞቻቸው በተጨማሪ አሰባሰቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ብንያማውያንም ከመላው የጊብዓ ነዋሪዎች መካከል ከተመረጡት ሰባት መቶ ሰዎች ሌላ፥ ሰይፍ የታጠቁ ሃያ ስድስት ሺህ ሰዎች በአንድ አፍታ ከየከተሞቻቸው በተጨማሪ አሰባሰቡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በዚያን ቀን ብንያማውያን፥ ከየከተሞቻቸው ኻያ ስድስት ሺህ መሣሪያ የታጠቁ ሰዎችን አሰባሰቡ፤ ይህም ከጊብዓ ኗሪዎች ከተመረጡት ከሰባት መቶ ሰዎች ሌላ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በዚያም ቀን ከየከተማው የመጡ የብንያም ልጆች ተቈጠሩ፥ ቁጥራቸውም ከጊብዓ ሰዎች ሌላ ሀያ ስድስት ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ነበሩ፥ ከጊብዓም ሰባት መቶ የተመረጡ ሰዎች ተቆጠሩ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 20:15
9 Referencias Cruzadas  

የጋድ ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው- በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥


ከጋድ ነገድ የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ አም​ስት ሺህ ስድ​ስት መቶ አምሳ ነበሩ።


የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም፥ ሠላሳ አም​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።


እነ​ዚህ የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሠላሳ ሁለት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ። በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የዮ​ሴፍ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።


የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር ሊዋጉ ከየ​ከ​ተ​ማ​ዎ​ቻ​ቸው ወደ ገባ​ዖን ተሰ​በ​ሰቡ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ተበ​ራቱ፤ በፊ​ተ​ኛ​ውም ቀን በተ​ሰ​ለ​ፉ​በት ስፍራ ደግ​መው ተሰ​ለፉ።


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የብ​ን​ያም ልጆች ሊገ​ጥ​ሙ​አ​ቸው ከገ​ባ​ዖን ወጡ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ደግሞ ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ሰዎ​ችን በም​ድር ላይ ገደሉ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ነበሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብን​ያ​ምን በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ጣላ​ቸው፤ በዚ​ያም ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብ​ን​ያም ሃያ አም​ስት ሺህ አንድ መቶ ሰዎ​ችን ገደሉ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos