ኤልያስም ሕዝቡን፥ “የበዓልን ነቢያት ያዙ፤ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳን የሚያመልጥ አይኑር፤” አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየወጋ ጣላቸው።
ዘኍል 25:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የእስራኤልን ሕዝቦች፥ “እናንተ እያንዳንዳችሁ ብዔል ፌጎርን የተከተሉትን ሰዎቻችሁን ግደሉ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም የእስራኤልን ዳኞች፣ “እያንዳንዳችሁ በኣል ፌጎርን በማምለክ የተባበሩትን ሰዎቻችሁን ግደሉ አላቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የእስራኤልን ዳኞች፦ “እናንተም እያንዳንዳችሁ ብዔልፌጎርን የተከተሉትን ሰዎቻችሁን ግደሉ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም ለእስራኤል መሪዎች “እያንዳንዳችሁ ከየነገዳችሁ በዓል ለሚባለው የፒዖር ጣዖት የሰገደውን ሰው ሁሉ ግደሉ” ብሎ ትእዛዝ አስተላለፈ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የእስራኤልን ዳኞች፦ እናንተ ሁሉ ብዔልፌጎርን የተከተሉትን ሰዎቻችሁን ግደሉ አላቸው። |
ኤልያስም ሕዝቡን፥ “የበዓልን ነቢያት ያዙ፤ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳን የሚያመልጥ አይኑር፤” አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየወጋ ጣላቸው።
አንተም ከሕዝቡ ሁሉ ኀያላን ሰዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን እውነተኞች ሰዎችን፥ ትዕቢትንም የሚጠሉ ሰዎችን ፈልግ። ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የዐሥርም አለቆችን ሹምላቸው።
ክፋተኞች ሰዎች ከእናንተ ዘንድ ወጥተው፦ ሄደን የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብለው የከተማቸውን ሰዎች አሳቱ ሲሉ ወሬ ብትሰማ፥
“የአባትህ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብራህ የምትተኛ ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ፥
እኛ እስከ ዛሬ ድረስ ከእርሱ ያልነጻንበት የፌጎር ኀጢአት ጥቂት ነውን? በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ወረደ።