La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 23:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በተ​ራ​ሮች ራስ ላይ ሆኜ አየ​ዋ​ለሁ፤ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ላይ ሆኜ እመ​ለ​ከ​ተ​ዋ​ለሁ፤ እነሆ፥ ብቻ​ውን የሚ​ቀ​መጥ ሕዝብ ነው፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል አይ​ቈ​ጠ​ርም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዐለታማ ተራሮች ጫፍ ሆኜ አየዋለሁ፤ በከፍታዎቹም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤ ተለይቶ የሚኖረውን፣ ራሱንም ከሌሎች ሕዝቦች ጋራ የማይቈጥረውን ሕዝብ አያለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በተራሮች ራስ ላይ ሆኜ አየዋለሁ፥ በኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤ እነሆ፥ ብቻውን የሚቀመጥ ሕዝብ ነው፥ በአሕዛብም መካከል አይቈጠርም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔ እነርሱን ከነዚህ ከፍተኛ አለቶች ላይ ሆኜ አያቸዋለሁ፤ ከኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከታቸዋለሁ፤ እነርሱ ለብቻቸው የሚኖሩ ሕዝብ ናቸው። እነርሱ ከሌሎች ሕዝቦች ይልቅ የተለዩ መሆናቸውን ያውቃሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በአምቦች ራስ ላይ ሆኜ አየዋለሁ፥ በኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤ እነሆ፥ ብቻውን የሚቀመጥ ሕዝብ ነው፥ በአሕዛብም መካከል አይቈጠርም።

Ver Capítulo



ዘኍል 23:9
15 Referencias Cruzadas  

ለራ​ሳ​ቸ​ውና ለል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ወስ​ደ​ዋል፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ዘር ከም​ድር አሕ​ዛብ ጋር ደባ​ል​ቀ​ዋል፤ አስ​ቀ​ድ​ሞም አለ​ቆ​ቹና ሹሞቹ በዚህ መተ​ላ​ለፍ መጀ​መ​ሪያ ሆነ​ዋል” አሉኝ።


በም​ድ​ርም ከአ​ለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝ​ብህ ተለ​ይ​ተን እን​ከ​ብር ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካል​ሄ​ድህ፥ እኔና ሕዝ​ብህ በአ​ንተ ዘንድ በእ​ው​ነት ሞገስ ማግ​ኘ​ታ​ችን በምን ይታ​ወ​ቃል?” አለው።


አንተ ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ ሆይ! እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተ​ንም ያሳ​ደ​ድ​ሁ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለ​ሁና፥ አን​ተን ግን ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ህም፤ በመ​ጠን እቀ​ጣ​ሃ​ለሁ፥ ያለ ቅጣ​ትም አል​ተ​ው​ህም።”


“ተነሡ፤ ዕረ​ፍት ወዳ​ለ​በት፥ ተዘ​ል​ሎም ወደ ተቀ​መ​ጠው፥ ደጅና መዝ​ጊያ፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያም ወደ​ሌ​ለው፥ ብቻ​ው​ንም ወደ ተቀ​መ​ጠው ሕዝብ ዝመቱ።


እነሆ አዝ​ዛ​ለሁ፤ እህ​ልም በመ​ንሽ እን​ደ​ሚ​ዘራ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል እዘ​ራ​ለሁ፤ ነገር ግን አን​ዲት ቅን​ጣት በም​ድር ላይ አት​ወ​ድ​ቅም።


በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።


ስለ​ዚ​ህም “ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተለ​ይ​ታ​ችሁ ውጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩ​ሳ​ንም አት​ቅ​ረቡ፥ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ልዑል አሕ​ዛ​ብን በከ​ፈ​ላ​ቸው ጊዜ፥ የአ​ዳ​ም​ንም ልጆች በለ​ያ​ቸው ጊዜ፥ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ቍጥር፥ አሕ​ዛ​ብን በየ​ድ​ን​በ​ራ​ቸው አቆ​ማ​ቸው።


እስ​ራ​ኤ​ልም ተማ​ምኖ፥ በያ​ዕ​ቆብ ምድር ብቻ​ውን፥ በስ​ን​ዴና በወ​ይን ምድር ይኖ​ራል፤ ሰማይ ከደ​መ​ናና ከጠል ጋር ለአ​ንተ ነው።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤