የእስራኤልን ልጆች በእንጀራና በውኃ አልተቀበሉአቸውምና፥ ይረግማቸውም ዘንድ በለዓምን ገዝተውባቸዋልና፤ ነገር ግን አምላካችን ርግማኑን ወደ በረከት መለሰው።
ዘኍል 23:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባላቅም በለዓምን፥ “ያደረግኽብኝ ምንድን ነው? ጠላቶችን ትረግምልኝ ዘንድ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ መባረክን ባረክሃቸው” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባላቅም በለዓምን፣ “እንዴት እንዲህ ታደርገኛለህ? ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ አመጣሁህ፤ አንተ ግን ባረክሃቸው እንጂ ምንም አላደረግህልኝም!” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “ያደረግህብኝ ምንድነው? ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ ፈጽመህ ባረክሃቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባላቅም በለዓምን “ይህ ያደረግህብኝ ምንድን ነው? እኔ ወደዚህ ያመጣሁህ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ነበር፤ አንተ ግን እነርሱን ከመመረቅ በቀር ምንም አላደረግህም” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባላቅም በለዓምን፦ ያደረግህብኝ ምንድር ነው? ጠላቶቼን ትረግምልኝ ዘንድ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ ፈጽመህ ባረክሃቸው አለው። |
የእስራኤልን ልጆች በእንጀራና በውኃ አልተቀበሉአቸውምና፥ ይረግማቸውም ዘንድ በለዓምን ገዝተውባቸዋልና፤ ነገር ግን አምላካችን ርግማኑን ወደ በረከት መለሰው።
እነሆ፥ ከግብፅ የወጣ ሕዝብ የምድርን ፊት ሸፈነ፤ በአቅራቢያዬም ተቀምጦአል፤ ምናልባት እወጋው፥ አሳድደውም ዘንድ እችል እንደ ሆነ አሁንም ና እርሱን ርገምልኝ።”
ክብርህን እጅግ ታላቅ አደርገዋለሁና፥ የተናገርኸውንም ሁሉ አደርግልሃለሁና ና፥ ይህን ሕዝብ ርገምልኝ ብሏል” አሉት።