| ዘኍል 23:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ባላቅም በለዓምን፦ ያደረግህብኝ ምንድር ነው? ጠላቶቼን ትረግምልኝ ዘንድ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ ፈጽመህ ባረክሃቸው አለው።Ver Capítulo አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ባላቅም በለዓምን፣ “እንዴት እንዲህ ታደርገኛለህ? ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ አመጣሁህ፤ አንተ ግን ባረክሃቸው እንጂ ምንም አላደረግህልኝም!” አለው።Ver Capítulo መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “ያደረግህብኝ ምንድነው? ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ ፈጽመህ ባረክሃቸው።”Ver Capítulo አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ባላቅም በለዓምን “ይህ ያደረግህብኝ ምንድን ነው? እኔ ወደዚህ ያመጣሁህ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ነበር፤ አንተ ግን እነርሱን ከመመረቅ በቀር ምንም አላደረግህም” አለው።Ver Capítulo የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ባላቅም በለዓምን፥ “ያደረግኽብኝ ምንድን ነው? ጠላቶችን ትረግምልኝ ዘንድ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ መባረክን ባረክሃቸው” አለው።Ver Capítulo |