አሕዛብ ይገዙልህ፤ አለቆችም ይስገዱልህ፤ ለወንድምህ ጌታ ሁን፤ የአባትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”
ዘኍል 22:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ከግብፅ የወጣ ሕዝብ የምድርን ፊት ሸፈነ፤ በአቅራቢያዬም ተቀምጦአል፤ ምናልባት እወጋው፥ አሳድደውም ዘንድ እችል እንደ ሆነ አሁንም ና እርሱን ርገምልኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ከግብጽ የወጣ ሕዝብ የምድሩን ገጽ አጥለቅልቆታል፤ ስለዚህ መጥተህ ርገምልኝ፤ ምናልባት ልዋጋቸውና ላባርራቸው የምችለው ከዚያ በኋላ ሊሆን ይችላል።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘እነሆ፥ ከግብጽ የወጣ ሕዝብ የምድርን ፊት ሸፈነ፥ ምናልባት ልወጋው ላሳድደውም እችል እንደሆነ አሁን ና እርሱን ርገምልኝ።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ከግብጽ የወጣ ሕዝብ ምድሪቱን ሸፍኖአታል፤ መጥተህ ብትረግምልኝ ምናልባት እነርሱን በጦርነት ተዋግቼ ላስወጣቸው እችል ይሆናል።’ ” |
አሕዛብ ይገዙልህ፤ አለቆችም ይስገዱልህ፤ ለወንድምህ ጌታ ሁን፤ የአባትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”
ባላቅም በለዓምን፥ “ያደረግኽብኝ ምንድን ነው? ጠላቶችን ትረግምልኝ ዘንድ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ መባረክን ባረክሃቸው” አለው።
በምሳሌም ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፦ “የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ከሜስጴጦምያ ጠርቶ አመጣኝ፤ ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን ተጣላልኝ” ብሎ።
ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፥ “በትርና ድንጋይ ይዘህ የምትመጣብኝ እኔ ውሻ ነኝን?” አለው። ዳዊትም፥ “የለም ከውሻ ትከፋለህ” አለው። ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን በአምላኮቹ ረገመው።