La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 21:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሐሴ​ቦ​ንም የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ንጉሥ የሴ​ዎን ከተማ ነበረ፤ እር​ሱም የፊ​ተ​ኛ​ውን የሞ​ዓ​ብን ንጉሥ ወግቶ ከአ​ሮ​ኤር እስከ አር​ኖን ድረስ ምድ​ሩን ሁሉ ወስዶ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሐሴቦን የቀድሞውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ እስከ አርኖን ድረስ ያለውን ምድሩን የወሰደበት የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሐሴቦንም የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረ፤ እርሱም የፊተኛውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ እስከ አርኖን ድረስ ምድሩን ሁሉ ከእጁ ወስዶ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሐሴቦን የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን መናገሻ ከተማ ነበረች፤ እርሱም ከሞአብ የቀድሞ ንጉሥ ጋር ተዋግቶ እስከ አርኖን ወንዝ ያለውን ምድር ሁሉ ወስዶበት ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሐሴቦንም የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረ፤ እርሱም የፊተኛውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ እስከ አርኖን ድረስ ምድሩን ሁሉ ከእጁ ወስዶ ነበር።

Ver Capítulo



ዘኍል 21:26
13 Referencias Cruzadas  

ሁለቱ ጡቶ​ችሽ እንደ ሁለት መንታ እንደ ሚዳቋ ግል​ገ​ሎች ናቸው።


አን​ገ​ትሽ እንደ ዝሆን ጥርስ ግንብ ነው፤ ዐይ​ኖ​ችሽ በሐ​ሴ​ቦን ውስጥ በብ​ዙ​ዎች ልጅ በሮች አጠ​ገብ እን​ዳሉ እንደ ውኃ ኵሬ​ዎች ናቸው፤ አፍ​ን​ጫሽ ወደ ደማ​ስቆ አፋ​ዛዥ እን​ደ​ሚ​መ​ለ​ከት እንደ ሊባ​ኖስ ግንብ ነው።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የሞ​አብ ፈውስ የለም፤ በሐ​ሴ​ቦን ላይ፥ “ኑ ሕዝብ እን​ዳ​ት​ሆን እና​ጥ​ፋት” ብለው ክፉ ነገ​ርን አስ​በ​ው​ባ​ታል። ፈጽሞ ትተ​ዋ​ለች፤ ከኋ​ላዋ ሰይፍ ይመ​ጣ​ልና።


“ሞአብ ፈር​ሳ​ለ​ችና አፈ​ረች፤ አል​ቅሱ፥ ጩኹም፤ ሞአብ እንደ ጠፋች በአ​ር​ኖን አውሩ።


ከሰ​ልፍ የሸሹ ከሐ​ሴ​ቦን ጥላ በታች ቆመ​ዋል፤ እሳት ከሐ​ሴ​ቦን፥ ነበ​ል​ባ​ልም ከሴ​ዎን ወጥ​ቶ​አል፤ የሞ​አ​ብ​ንም ማዕ​ዘን፥ የሚ​ጮኹ ልጆ​ች​ንም ራስ በል​ቶ​አል።


እስ​ራ​ኤ​ልም እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ሁሉ ወሰደ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በአ​ሞ​ራ​ው​ያን ከተ​ሞች ሁሉ፥ በሐ​ሴ​ቦ​ንና በመ​ን​ደ​ሮቹ ሁሉ ተቀ​መጠ።


ስለ​ዚህ የም​ሳሌ ሰዎች እን​ዲህ ብለው ይና​ገ​ራሉ፦ “ወደ ሐሴ​ቦን ኑ፤ የሴ​ዎን ከተማ ይመ​ሥ​ረት፤ ይገ​ንባ፤


በሐ​ሴ​ቦን ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፥ በአ​ስ​ጣ​ሮ​ትና በኤ​ድ​ራ​ይን ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረ​ው​ንም የባ​ሳ​ንን ንጉሥ ዐግን ከገ​ደ​ሉት በኋላ፥


ድን​በ​ራ​ቸ​ውም በአ​ር​ኖን ሸለቆ ዳር ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ በሸ​ለ​ቆው መካ​ከል ያለ​ችው ከተማ፥ ሜሶ​ርም ሁሉ፥


ሐሴ​ቦን፥ በሜ​ሶ​ርም ያሉት ከተ​ሞች ሁሉ፥ ዲቦን፥ ባሞ​ት​በ​ዐል፥ ቤት​በ​አ​ል​ም​ዖን፥


ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ኢያ​ዜ​ርና የገ​ለ​ዓድ ከተ​ሞች ሁሉ፥ የአ​ሞ​ንም ልጆች ምድር እኩ​ሌታ በራ​ባት ፊት እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አሮ​ዔር ድረስ፥


ሐሴ​ቦ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኢያ​ዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ።


እስ​ራ​ኤ​ልም በሐ​ሴ​ቦ​ንና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በአ​ሮ​ዔ​ርና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በአ​ር​ኖ​ንም አቅ​ራ​ቢያ ባሉት ከተ​ሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀ​ምጦ በነ​በረ ጊዜ፥ በዚያ ዘመን ስለ ምን አላ​ዳ​ን​ሃ​ቸ​ውም ነበር?