La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 21:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሴዎ​ንም እስ​ራ​ኤል በወ​ሰኑ ላይ ያልፉ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ሴዎ​ንም ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ለመ​ው​ጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፤ ወደ ኢያ​ሶ​ንም መጣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ተዋ​ጋ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሴዎን ግን እስራኤል በግዛቱ ውስጥ እንዲያልፍ አልፈቀደም፤ ሰራዊቱን በሙሉ አሰባስቦ እስራኤልን ለመውጋት ወደ ምድረ በዳው ወጣ፤ ያሀጽ እንደ ደረሰም ከእስራኤል ጋራ ጦርነት ገጠመ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሴዎንም እስራኤል በምድሩ ላይ እንዳያልፍ ከለከለ፤ ሴዎንም ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ እስራኤልንም ለመውጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፥ ወደ ያሀጽም መጣ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሲሖን ግን የእስራኤል ሕዝብ በግዛቱ አልፈው እንዲሄዱ አልፈቀደላቸውም፤ እንዲያውም ሠራዊቱን ሁሉ ሰብስቦ በበረሓ ውስጥ ወዳለችው ወደ ያሀጽ በመሄድ በእስራኤላውያን ላይ ጦርነት አደረገ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሴዎንም እስራኤል በምድሩ ላይ ያልፍ ዘንድ እንቢ አለ፤ ሴዎንም ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ እስራኤልንም ለመውጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፥ ወደ ያሀጽም መጣ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ።

Ver Capítulo



ዘኍል 21:23
11 Referencias Cruzadas  

ሐሴ​ቦ​ንና ኤል​ያሊ ጮኹ፤ ድም​ፃ​ቸ​ውም እስከ ያሳ ድረስ ይሰ​ማል፤ ስለ​ዚህ የሞ​ዓብ ወገብ ይታ​መ​ማል።


ፍርድ ይመ​ጣል፤ በሜ​ሶር ምድር፥ በኬ​ሎን፥ በያ​ሳና፥ በሜ​ፍ​ዓት ላይ፤


ከሐ​ሴ​ቦን ጩኸት እስከ ኤሊ​ያ​ሊና እስከ ኢያሳ ድረስ ድም​ፃ​ቸ​ውን ሰጥ​ተ​ዋል፤ ከሴ​ጎር እስከ ሖሮ​ና​ይ​ምና እስከ ዔግ​ላት ሺሊ​ሺያ ድረስ ይደ​ር​ሳል፤ የኔ​ም​ሬም ውኃ ደር​ቋ​ልና።


እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብር​ታ​ቱም እንደ ወይራ ዛፍ የነ​በ​ረ​ውን አሞ​ራ​ዊ​ውን ከፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋሁ፤ ፍሬ​ው​ንም ከላዩ፥ ሥሩ​ንም ከታቹ አጠ​ፋሁ።


የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ “በእኔ በኩል አታ​ል​ፍም፤ ይህ ካል​ሆነ ግን እን​ዋ​ጋ​ለን፤ በጦ​ርም እቀ​በ​ልህ ዘንድ እወ​ጣ​ለሁ” አለው።


የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ እስ​ራ​ኤል በዳ​ር​ቻው እን​ዲ​ያ​ልፍ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤል ከእ​ርሱ ተመ​ለሰ።


ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ቱት፥ በሐ​ሴ​ቦን ተቀ​ምጦ በነ​በ​ረው በአ​ሞ​ሬ​ዎን ንጉሥ በሴ​ዎን ምድር፥ በቤተ ፌጎር አቅ​ራ​ቢያ ባለው ሸለቆ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ፤


ባሳን፥ ቀዲ​ሞት፥ ሜፍዓ፥


ሴዎ​ንም እስ​ራ​ኤል በድ​ን​በሩ እን​ዲ​ያ​ልፍ እንቢ አለ፤ ነገር ግን ሴዎን ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ በኢ​ያ​ሴ​ርም ሰፈረ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር ተዋጋ።