ዘኍል 21:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ሲሖን ግን የእስራኤል ሕዝብ በግዛቱ አልፈው እንዲሄዱ አልፈቀደላቸውም፤ እንዲያውም ሠራዊቱን ሁሉ ሰብስቦ በበረሓ ውስጥ ወዳለችው ወደ ያሀጽ በመሄድ በእስራኤላውያን ላይ ጦርነት አደረገ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ሴዎን ግን እስራኤል በግዛቱ ውስጥ እንዲያልፍ አልፈቀደም፤ ሰራዊቱን በሙሉ አሰባስቦ እስራኤልን ለመውጋት ወደ ምድረ በዳው ወጣ፤ ያሀጽ እንደ ደረሰም ከእስራኤል ጋራ ጦርነት ገጠመ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ሴዎንም እስራኤል በምድሩ ላይ እንዳያልፍ ከለከለ፤ ሴዎንም ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ እስራኤልንም ለመውጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፥ ወደ ያሀጽም መጣ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ሴዎንም እስራኤል በወሰኑ ላይ ያልፉ ዘንድ አልፈቀደም፤ ሴዎንም ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፤ እስራኤልንም ለመውጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፤ ወደ ኢያሶንም መጣ፤ እስራኤልንም ተዋጋቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ሴዎንም እስራኤል በምድሩ ላይ ያልፍ ዘንድ እንቢ አለ፤ ሴዎንም ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ እስራኤልንም ለመውጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፥ ወደ ያሀጽም መጣ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ። Ver Capítulo |