ይቈጠሩ ዘንድ የሚያልፉት ሁሉ የሚሰጡት ይህ ነው፤ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን የሰቅል ግማሽ ይሰጣል። ሰቅሉም ሃያ አቦሊ ነው፤ የሰቅሉም ግማሽ ለእግዚአብሔር ቍርባን ነው።
ዘኍል 18:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንድ ወር የሆነው ልጅ ዋጋው በቤተ መቅደስ ሚዛን አምስት ሰቅል ነው። ይኸውም ሃያ አቦሊ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህም አንድ ወር ሲሆናቸው ሃያ ጌራ በሚመዝነው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ልክ፣ በተወሰነው በመዋጃው ዋጋ በዐምስት ሰቅል ጥሬ ብር ትዋጀዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአንድ ወር ጀምሮ የምትዋጀውን እንደ ግምትህ ትዋጀዋለህ፤ ግምቱም እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን አምስት ሰቅል ይሆናል፤ እርሱም ሀያ አቦሊ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ወር የሞላቸው ሕፃናት በይፋ በተመደበው ዋጋ መሠረት አምስት ሰቅል ጥሬ ብር የቤዛ ዋጋ ተከፍሎላቸው ሊዋጁ ይችላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአንድ ወር ጀምሮ የምትቤዠውን እንደ ግምትህ ትቤዠዋለህ፤ ግምቱም እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን አምስት ሰቅል ይሆናል፤ እርሱም ሀያ አቦሊ ነው። |
ይቈጠሩ ዘንድ የሚያልፉት ሁሉ የሚሰጡት ይህ ነው፤ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን የሰቅል ግማሽ ይሰጣል። ሰቅሉም ሃያ አቦሊ ነው፤ የሰቅሉም ግማሽ ለእግዚአብሔር ቍርባን ነው።
የተሰጠው ወርቅ ሁሉ፥ ለድንኳኑ ሥራ ሁሉ የተደረገው ወርቅ፥ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ሃያ ዘጠኝ መክሊት ሰባት መቶ ሠሳሳ ሰቅል ነበረ።
ከሰው እስከ እንስሳ ቢሆን፥ ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ሥጋ ሁሉ፥ መጀመሪያ የሚወለድ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትቤዠዋለህ፤ ያልነጹትንም እንስሳት በኵራት ትቤዣለህ።
ነገር ግን የላሞቹን በኵራት፥ ወይም የበጎቹን በኵራት፥ የፍየሎችንም በኵራት አትቤዥም፤ ቅዱሳን ናቸውና፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ ትረጨዋለህ፤ ስባቸውንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን መሥዋዕት ታደርገዋለህ።