La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 17:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ንገ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት አንድ አንድ በትር፥ ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም ከየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በት​ሮች ውሰድ፤ የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱ​ንም ስም በየ​በ​ትሩ ላይ ጻፍ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ለእስራኤላውያን ንገራቸውና ከየነገዱ አለቆች አንዳንድ፣ በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት በትር ተቀበል፤ የያንዳንዱንም ሰው ስም በየበትሩ ላይ ጻፈው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ለእስራኤል ልጆች ተናገር፥ ከእነርሱም ከእያንዳንዱ ከየአባቶቻቸው ቤት አንድ አንድ በትር፥ ከአለቆቻቸው ሁሉ ከየአባቶቻቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በትሮች፥ ውሰድ፤ የእያንዳንዱንም ስም በየበትሩ ላይ ጻፍ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“የእስራኤል ሕዝብ ከያንዳንዱ የነገድ መሪ አንዳንድ በትር ተቀብለው ዐሥራ ሁለት በትሮች እንዲሰጡህ ጠይቃቸው፤ የእያንዳንዱንም ስም በበትሩ ላይ ጻፍ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፥ ከእነርሱም ከእያንዳንዱ ከየአባቶቻቸው ቤት አንድ አንድ በትር፥ ከአለቆቻቸው ከየአባቶቻቸው ቤት አሥራ ሁለት በትሮች፥ ውሰድ፤ የእያንዳንዱንም ስም በየበትሩ ላይ ጻፍ።

Ver Capítulo



ዘኍል 17:2
18 Referencias Cruzadas  

መን​ግ​ሥት ከይ​ሁዳ አይ​ጠ​ፋም፤ ምስ​ፍ​ናም ከአ​ብ​ራኩ፥ ለእ​ርሱ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እስ​ኪ​ያ​ገኝ ድረስ፤ የአ​ሕ​ዛብ ተስ​ፋ​ቸው እርሱ ነውና፤


በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤት ለተ​ቈ​ጠሩ ካህ​ናት፥ ከሃያ ዓመ​ትም ወደ ላይ ላሉ በየ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸ​ውና በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ለተ​ቈ​ጠሩ ሌዋ​ው​ያን፥


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ታላቅ ናት፥ በፈ​ቃ​ዱም ሁሉ የተ​ፈ​ለ​ገች ናት።


ደስ​ተ​ኞ​ችም ሆን።


የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ታቦት፥


ይህ​ች​ንም ተአ​ም​ራት የም​ታ​ደ​ር​ግ​ባ​ትን በትር በእ​ጅህ ያዝ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይህ በእ​ጅህ ያለው ምን​ድን ነው?” አለው። እር​ሱም፥ “በትር ነው” አለ።


ከተ​መ​ረ​ጡት ጫፎ​ች​ዋም በትር እሳት ወጣች፤ ፍሬ​ዋ​ንም በላች፤ የነ​ገ​ሥ​ታ​ትም በትር ይሆን ዘንድ የበ​ረታ በትር የለ​ባ​ትም።” ይህ ሙሾ ነው፤ ለል​ቅ​ሶም ይሆ​ናል።


ወግ​ተሽ ትገ​ድሊ ዘንድ፥ ታብ​ረ​ቀ​ር​ቂም ዘንድ ተሳዪ፤ ትገ​ድ​ሊም ዘንድ፥ ዕን​ጨ​ቱ​ንም ሁሉ ትጥዪ ዘንድ ጨክኚ፤


እው​ነት ሆኖ​አ​ልና፤ የራቁ ሕዝቤ ምን ሆኑ? የሉ​ምና፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


ለየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ወገን አንድ በትር ይሰ​ጣ​ሉና በሌዊ በትር ላይ የአ​ሮ​ንን ስም ጻፍ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ ድን​ኳ​ኑን ፈጽሞ በተ​ከ​ለ​ባት፥ እር​ስ​ዋ​ንና ዕቃ​ዋን ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት፥ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንና ዕቃ​ው​ንም ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት ቀን፥