ሲገድሉም እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግንባሬ ተደፍቼ፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን?” ብዬ ጮኽሁ።
ዘኍል 16:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በሰማ ጊዜ በግንባሩ ወደቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም ይህን ሲሰማ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በሰማ ጊዜ በግምባሩ ወድቆ ሰገደ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም ይህን በሰማ ጊዜ በግንባሩ ወድቆ ጸለየ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በሰማ ጊዜ በግምባሩ ወደቀ፤ |
ሲገድሉም እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግንባሬ ተደፍቼ፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን?” ብዬ ጮኽሁ።
እነርሱም በግንባራቸው ወድቀው፥ “የነፍስና የሥጋ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንድ ሰው ኀጢአት ቢሠራ የእግዚአብሔር ቍጣ በማኅበሩ ላይ ይሆናልን?” አሉ።
ለቆሬም ለማኅበሩም ሁሉ እንዲህ አላቸው፥ “ነገ እግዚአብሔር የእርሱ የሚሆኑትን፥ ቅዱሳንም የሆኑትን ያያል፥ ያውቃልም፤ የመረጣቸውንም ሰዎች ወደ እርሱ ያቀርባቸዋል።
ሙሴና አሮንም ከማኅበሩ ፊት ወደ ምስክሩ ድንኳን ዳጃፍ ሄደው በግንባራቸው ወደቁ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠላቸው።
ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፤ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግንባራቸው ተደፉ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።