ሙሴም አሮንን፥ “ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ ‘ማንጐራጐራችሁን ሰምቶአልና ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ’ በል” አለው።
ዘኍል 16:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ቆሬን አለው፥ “ማኅበርህን ለይ፤ ነገ አንተ፥ ማኅበርህም ሁሉ፥ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ዝግጁዎች ሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም ቆሬን እንዲህ አለው፤ “አንተና ተከታዮችህ እንዲሁም አሮን ነገ በእግዚአብሔር ፊት ትቀርባላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ቆሬን እንዲህ አለው፦ “ነገ አንተ፥ አንተንም የሚከተሉህ ሁሉ፥ አሮንም በጌታ ፊት ተገኙ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ቆሬን እንዲህ አለው፦ “ነገ አንተና ሁለት መቶ ኀምሳ ተባባሪዎችህ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን እንድትመጡ፤ አሮንም እዚያው ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ቆሬን፦ ነገ አንተ፥ ወገንህም ሁሉ፥ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ሁኑ፤ |
ሙሴም አሮንን፥ “ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ ‘ማንጐራጐራችሁን ሰምቶአልና ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ’ በል” አለው።
እግዚአብሔርም ወዲያው ሙሴንና አሮንን ማርያምንም፥ “ሦስታችሁ ወደ ምስክሩ ድንኳን ኑ ብሎ ተናገረ፤ ሦስቱም ወደ ምስክሩ ድንኳን ወጡ።
ሙሴም እጅግ አዘነ፤ እግዚአብሔርንም አለው፥ “ወደ መሥዋዕታቸው አትመልከት፤ እኔ ከእነርሱ አንዳችም ተመኝቼ አልወሰድሁም፤ ከእነርሱም አንድ ሰው አልበደልሁም።”
ሁላችሁም ጥናዎቻችሁን ውሰዱ፤ ዕጣንም አድርጉባቸው፤ እያንዳንዳችሁም ሁለት መቶ አምሳ ጥናዎቻችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት አምጡ፤ አንተ ደግሞ አሮንም ጥናዎቻችሁን አምጡ” አለው።
እነሆኝ፥ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንንስ አህያ ወሰድሁ? ማንንስ ሸነገልሁ? በማንስ ላይ ግፍ አደረግሁ? ነጠላ ጫማ እንኳን ቢሆን ከማን እጅ መማለጃ ተቀበልሁ? መስክሩብኝ፤ እኔ እመልስላችኋለሁ።”
አሁንም ቁሙ፤ በእግዚአብሔርም ፊት እፋረዳችኋለሁ፤ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ያደረገውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሁሉ እነግራችኋለሁ።