ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ ሰው በሰው ላይ፥ ሰውም በባልንጀራው ላይ ይገፋፋል፤ ብላቴናውም በሽማግሌው ላይ፥ የተጠቃውም በከበርቴው ላይ ይታበያል።
ዘኍል 16:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የኤልያብን ልጆች ዳታንንና አቤሮንን እንዲጠሩአቸው ላከ፤ እነርሱም፥ “አንመጣም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሙሴ የኤልያብን ልጆች ዳታንና አቤሮንን አስጠራቸው፤ እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፤ “እኛ አንመጣም! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የኤልያብን ልጆች ዳታንና አቤሮንን እንዲጠሩአቸው ላከ፤ እነርሱም እንዲህ አሉ፦ “አንመጣም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሙሴ የኤልያብ ልጆች የሆኑትን ዳታንንና አቤሮንን ልኮ አስጠራ፤ እነርሱ ግን “አንመጣም!” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የኤልያብን ልጆች ዳታንና አቤሮንን እንዲጠሩአቸው ላከ፤ እነርሱም፦ አንመጣም፤ |
ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ ሰው በሰው ላይ፥ ሰውም በባልንጀራው ላይ ይገፋፋል፤ ብላቴናውም በሽማግሌው ላይ፥ የተጠቃውም በከበርቴው ላይ ይታበያል።
የሌዊም ልጅ የቀዓት ልጅ የይስዓር ልጅ ቆሬ ከኤልያብ ልጆች ከዳታንና ከአቤሮን፥ ከሮቤልም ልጅ ከፋሌት ልጅ ከአውናን ጋር ተናገረ።
ስለዚህም አንተና ማኅበርህ ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ተሰብስባችኋል፤ በእርሱም ላይ ታጕረመርሙ ዘንድ አሮን ማንነው?”
በምድረ በዳ ትገድለን ዘንድ፥ በእኛም ላይ አለቃችን ትሆን ዘንድ ወተትና ማር ከምታፈስሰው ምድር ያወጣኸን አነሰህን?