“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ሳያውቅ በእግዚአብሔር ፊት ኀጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥
ዘኍል 15:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ብትበድሉም፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ያዘዛቸውን እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘እንግዲህ ካለማወቅ የተነሣ እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጣቸው ትእዛዞች አንዱን ሳትፈጽሙ ብትቀሩ፣ ይህም ማለት መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነገር ግን ስሕተት ባለማወቅ ብትፈጽሙ፥ ጌታም ለሙሴ ያዘዛቸውን እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ምናልባት እናንተ ሆን ብላችሁ ሳይሆን ባለማወቅ እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጠው ትእዛዞች መካከል አንዱን ሳትጠብቁ ብትቀሩ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብትስቱም፥ እግዚአብሔርም ለሙሴ ያዘዛቸውን እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፥ |
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ሳያውቅ በእግዚአብሔር ፊት ኀጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥
“መኰንንም ኀጢአትን ቢሠራ፥ ሳያውቅም እግዚአብሔር አምላኩ፦ አትሥራ ያለውን ትእዛዝ ቢተላለፍ፥ እንዲህም ቢበድል፥
“ከሀገሩም ሕዝብ አንድ ሰው ኀጢአትን ሳያውቅ ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥራ ያለውን ትእዛዝ ቢተላለፍ፥ ቢበድልም፥
ካህኑም ከእነዚያ በአንዳቸው ስለ ሠራው ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል። የተረፈውም እንደ እህሉ ቍርባን ለካህኑ ይሆናል።”
እግዚአብሔር ካዘዘበት ከፊተኛው ቀን ጀምሮ ወደ ፊትም እስከ ልጅ ልጃችሁ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንደ አዘዛችሁ ባታደርጉ፥