“የእስራኤልን ልጆች ማንጐራጐር ሰማሁ፦ ማታ ሥጋን ትበላላችሁ፤ ማለዳም እንጀራን ትጠግባላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው።”
ዘኍል 14:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሚያጕረመርሙብኝን እኒህን ክፉ ማኅበር እስከ መቼ እታገሣቸዋለሁ? ስለ እናንተ በእኔ ላይ የሚያጕረመርሙትን የእስራኤል ልጆች ማጕረምረምን ሰማሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህ ክፉ ማኅበረ ሰብ በእኔ ላይ የሚያጕረመርመው እስከ መቼ ነው? የእነዚህን ነጭናጮች እስራኤላውያን ማጕረምረም ሰምቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሚያጉረመርምብኝን ይህን ክፉ ማኅበር እስከ መቼ እታገሠዋለሁ? በእኔ ላይ የሚያጉረመርሙትን የእስራኤልን ልጆች ማጉረምረም ሰምቻለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነዚህ ክፉዎች የሆኑ ሰዎች በእኔ ላይ የሚያጒረመርሙት እስከ መቼ ነው? እነዚህ አጒረምራሚዎች እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ሰምቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያጕረመርምብኝን ይህን ክፉ ሕዝብ እስከ መቼ እታገሠዋለሁ? በእኔ ላይ የሚያጕረመርሙትን የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ሰማሁ። |
“የእስራኤልን ልጆች ማንጐራጐር ሰማሁ፦ ማታ ሥጋን ትበላላችሁ፤ ማለዳም እንጀራን ትጠግባላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው።”
የእግዚአብሔርንም ክብር ጥዋት ታያላችሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ያንጐራጐራችሁትን ሰምቶአልና፤ በእኛም ላይ የምታንጐራጕሩ እኛ ምንድን ነን?” አሉ።
ሙሴም አሮንን፥ “ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ ‘ማንጐራጐራችሁን ሰምቶአልና ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ’ በል” አለው።
ሕዝቡም በክፋት በእግዚአብሔር ፊት አጕረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ሰምቶ ተቈጣ፤ እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ በእነርሱ ላይ ነደደች፤ ከሰፈሩም አንዱን ወገን በላች።
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “እኒህ ሕዝብ እስከ መቼ ያስቈጡኛል? በፊታቸውስ ባደረግሁት ተአምራት ሁሉ እስከ መቼ አያምኑብኝም?