ዘኍል 11:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ከመቃብረ ፍትወት ወደ አሴሮት ተጓዙ፤ በአሴሮትም ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡም ከቂብሮት ሃታአባ ወደ ሐጼሮት ተጕዘው እዚያው ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ከኬብሮን-ሐታማ ወደ ሐጼሮት ተጓዙ በሐጼሮትም ተቀመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ሕዝቡ ወደ ሐጼሮት ተጒዘው በዚያ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም ከምኞት መቃብር ወደ ሐጼሮት ተጓዙ በሐጼሮትም ተቀመጡ። |
በዮርዳኖስ ማዶ በምድረ በዳ፥ በምዕራብ በኩል በኤርትራ ባሕር አጠገብ በፋራንና በጦፌል፥ በላባንና በአውሎን፥ በካታኪሪሲያም መካከል፥ ሙሴ ለእስራኤል ሁሉ፥ የነገራቸው ቃላት እኒህ ናቸው።