የጐመጁ ሕዝብ በዚያ ተቀብረዋልና የዚያ ስፍራ ስም “መቃብረ ፍትወት” ተብሎ ተጠራ።
ሌላ ምግብ ለማግኘት የጐመጁትን ሰዎች በዚያ ስለ ቀበሯቸው የቦታው ስም “ቂብሮት ሃታአባ” ተባለ።
እንግዲህ የጐመጀውን ሕዝብ በዚያ ቀብረውታልና የዚያ ስፍራ ስም ኬብሮን-ሐታማ ተብሎ ተጠራ።
በሥጋ አምሮት የሞቱትን ሕዝብ እዚያ ቀብረዋቸው ስለ ነበር የዚያ ስፍራ ስም “የምኞት መቃብር” ተባለ፤
የጐመጁ ሕዝብ በዚያ ተቀብረዋልና የዚያ ስፍራ ስም የምኞት መቃብር ተብሎ ተጠራ።
ሕዝቡም ከመቃብረ ፍትወት ወደ አሴሮት ተጓዙ፤ በአሴሮትም ተቀመጡ።
ከሲና ምድረ በዳም ተጕዘው በምኞት መቃብር ሰፈሩ።
ከምኞት መቃብርም ተጕዘው በአቤሮት ሰፈሩ።
እነርሱ እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ ክፉ እንዳንመኝ እነርሱ ለእኛ ምሳሌ ሆኑልን።
“በውዕየት፥ በፈተናም በምኞት መቃብርም እግዚአብሔርን አስቈጣችሁት።