La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 11:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴም፥ “እኔ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያለሁ ሕዝብ ስድ​ስት መቶ ሺህ እግ​ረኛ ናቸው፤ አን​ተም፦ ሥጋን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ወር ሙሉም ይበ​ሉ​ታል አልህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሙሴ ግን እንዲህ አለ፤ “እነሆ እኔ በስድስት መቶ ሺሕ እግረኛ መካከል እገኛለሁ፤ አንተ ደግሞ ‘ወር ሙሉ የሚበሉትን ሥጋ እኔ እሰጣቸዋለሁ’ ብለሃል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ሙሴ እንዲህ አለ፦ “እኔ በመካከላቸው ሆኜ በእኔ ዘንድ ያሉት ሰዎች ሲቈጠሩ ስድስት መቶ ሺህ እግረኛ ናቸው፤ አንተም፦ ‘ወር ሙሉ የሚበሉትን ሥጋ እኔ እሰጣቸዋለሁ’ አልህ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሙሴም ለእግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ እኔ ስድስት መቶ ሺህ ሕዝብ በመምራት ላይ እገኛለሁ፤ ለአንድ ወር የሚበቃ ሥጋ ልትሰጣቸው ቃል ገብተሃል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሙሴም፦ እኔ በመካከላቸው ያለሁ ሕዝብ ስድስት መቶ ሺህ እግረኛ ናቸው፤ አንተም፦ ወር ሙሉ የሚበሉትን ሥጋ እኔ እሰጣቸዋለሁ አልህ።

Ver Capítulo



ዘኍል 11:21
9 Referencias Cruzadas  

ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ቡሩ​ክም ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ባ​ር​ኩ​ህ​ንም እባ​ር​ካ​ለሁ፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከራ​ምሴ ተነ​ሥ​ተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ከጓዝ ጋር ካሉት ሌላ ስድ​ስት መቶ ሺህ ሰው የሚ​ያ​ህል እግ​ረኛ ነበረ።


እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሰው አንድ አንድ ዲድ​ር​ክም አዋጣ፤ አንድ ዲድ​ር​ክም እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን የሰ​ቅል ግማሽ ነው፤ ይህም የተ​ዋ​ጣው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ከተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ ስድ​ስት መቶ ሦስት ሺህ አም​ስት መቶ አምሳ ሰዎች ነበረ።


የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሁሉ ስድ​ስት መቶ ሦስት ሺህ አም​ስት መቶ አምሳ ነበሩ።


በፊቴ ያለ​ቅ​ሳ​ሉና፦ የም​ን​በ​ላ​ውን ሥጋ ስጠን ይላ​ሉና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ የም​ሰ​ጠው ሥጋ ከየት አለኝ?


ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ያለ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንቃ​ች​ኋ​ልና፥ በፊ​ቱም፦ ለምን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኸን? ብላ​ችሁ አል​ቅ​ሳ​ች​ኋ​ልና በአ​ፍ​ን​ጫ​ችሁ እስ​ኪ​ወጣ መር​ዝም እስ​ኪ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ድረስ ወር ሙሉ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።”


የበ​ሬና የበግ መንጋ ቢታ​ረድ፥ የባ​ሕር ዓሣ ሁሉ ቢሰ​በ​ሰብ ይበ​ቃ​ቸ​ዋ​ልን?” አለ።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች የተ​ቈ​ጠሩ እነ​ዚህ ናቸው፤ ከየ​ሰ​ፈሩ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ ስድ​ስት መቶ ሦስት ሺህ አም​ስት መቶ አምሳ ነበሩ።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የተ​ቈ​ጠ​ሩት እነ​ዚህ ናቸው፤ ስድ​ስት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።