እግዚአብሔርም አብራምን አለው፥ “ከሀገርህ፥ ከዘመዶችህም፥ ከአባትህም ቤት ተለይተህ ውጣ፤ እኔ ወደማሳይህም ምድር ሂድ።
ዘኍል 10:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “አልሄድም፥ ነገር ግን ወደ ሀገሬና ወደ ዘመዶች እመለሳለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም መልሶ፣ “ይህስ አይሆንም፤ አልሄድም፤ ወደ አገሬና ወደ ወገኖቼ ተመልሼ እሄዳለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “አልሄድም፥ ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሖባብም “አይሆንም፤ እኔ ወደ ትውልድ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ አልሄድም፥ ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ አለው። |
እግዚአብሔርም አብራምን አለው፥ “ከሀገርህ፥ ከዘመዶችህም፥ ከአባትህም ቤት ተለይተህ ውጣ፤ እኔ ወደማሳይህም ምድር ሂድ።
“ነገር ግን ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፤ ወደ አንደኛው ቀርቦ ‘ልጄ ሆይ! ዛሬ ሂድና በወይኔ አትክልት ሥራ፤’ አለው።
“ወደ እኔ የሚመጣ፥ ሊከተለኝም የሚወድ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሰውነት እንኳ ቢሆን የማይጠላ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ በሥጋ የምናውቀው የለም፤ ክርስቶስንም በሥጋ ብናውቀው አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ የምናውቀው አይደለም።
እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፤ ተስፋቸውንም አላገኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይተው እጅ ነሱኣት፤ በምድሪቱም ላይ እነርሱ እንግዶችና መጻተኞች እንደ ሆኑ ዐወቁ።
አብርሃም በተጠራ ጊዜ ርስት አድርጎ ይወርሰው ዘንድ ወዳለው ሀገር ለመሄድ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚደርስም ሳያውቅ ሄደ።
የቄናዊው የሙሴ አማት የዮባብ ልጆችም ከዘንባባ ከተማ ተነሥተው ከዓራድ በአዜብ በኩል ወዳለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወደ ይሁዳ ልጆች ሄደው ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ።