ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር ቤት ከሚመጣው ገንዘብ ለእግዚአብሔር ቤት የሚሆኑ የብር መዝጊያዎች፥ ጽዋዎችና ጕጠቶች፥ ድስቶችም፥ መለከቶችም፥ የወርቅና የብር ዕቃዎችም አልተሠሩም ነበር።
ዘኍል 10:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሁለት የብር መለከቶች አስጠፍጥፈህ ለአንተ አድርግ፤ ማኅበሩን ለመጥራት ከሰፈራቸውም ለማስጓዝ ይሁኑልህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከተቀጠቀጠ ብር ሁለት መለከት አብጅ፤ ማኅበረ ሰቡን ለመጥሪያና ከሰፈራቸው እንዲነሡም ለመቀስቀሻ አድርጋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሁለት የብር መለከቶች ሥራ፤ እነርሱንም ተቀጥቅጦ በሚሠራ ሥራ ለራስህ አብጃቸው፤ ማኅበሩን ለመጥራት ከሰፈራቸውም ተነሥተው እንዲጓዙ ለመቀስቀስ ተጠቀምባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሕዝቡን በአንድነት ለመሰብሰብም ሆነ ከሰፈር ለመቀስቀስ የሚያገለግሉ ሁለት መለከቶችን ከተቀጠቀጠ ብር ሥራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለት የብር መለከቶች አጠፍጥፈህ ለአንተ አድርግ፤ ማኅበሩን ለመጥራት ከሰፈራቸውም ለማስጓዝ ይሁኑልህ። |
ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር ቤት ከሚመጣው ገንዘብ ለእግዚአብሔር ቤት የሚሆኑ የብር መዝጊያዎች፥ ጽዋዎችና ጕጠቶች፥ ድስቶችም፥ መለከቶችም፥ የወርቅና የብር ዕቃዎችም አልተሠሩም ነበር።
መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፥ ከአሳፍና ከኤማን፥ ከኤዶትምም ልጆች ጋር ወንድሞቻቸውም፥ ጥሩ በፍታ ለብሰው ጸናጽልና ከበሮ፥ መሰንቆም እየመቱ በመሠዊያው አጠገብ በምሥራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ ከእነርሱም ጋር መቶ ሃያ ካህናት መለከት ይነፉ ነበር።
“መቅረዝንም ከጥሩ ወርቅ አድርግ፤ የመቅረዙም እግሩና ቅርንጫፎቹ የተቀጠቀጠ ሥራ ይሁን፤ ጽዋዎቹም፥ ጕብጕቦቹም፥ አበቦቹም አንድነት በእርሱ ይደረጉበት።
መልካሙን የስንዴ ዱቄት ብታመጡ እንኳ ከንቱ ነው፤ ዕጣናችሁ በእኔ ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ መባቻዎቻችሁንና ሰንበቶቻችሁን፥ ታላቋን፥ ቀናችሁን፥ ጾማችሁንና ሥራ መፍታታችሁን አልወድም።
በይሁዳ ዘንድ ተናገሩ፤ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩና፦ በሀገሪቱ ላይ መለከት ንፉ በሉ፤ ጮኻችሁም፦ ሁላችሁ ተሰብሰቡ፤ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ በሉ።
በብብታቸው እንደ መሬት፤ በእግዚአብሔርም ቤት እንደ ንስር ይመጣል። ቃል ኪዳኔን ተላልፈዋልና፥ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና።
ጾምን ቀድሱ፤ ምህላንም ዐውጁ፤ ሽማግሌዎቹንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም በአንድነት ጩኹ።
በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ ዐዋጅ ንገሩ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይደንግጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና።