ዘኍል 1:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምናሴ ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች- እንደ እየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዮሴፍ ልጆች፦ ከኤፍሬም ዝርያ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከዮሴፍ ልጆች፥ የኤፍሬም ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለው፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዮሴፍ ልጆች፥ የኤፍሬም ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸውና በየአባቶቻቸው ቤቶች እንደየስማቸው ቊጥር ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዮሴፍ ልጆች፥ የኤፍሬም ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥ |
ለዮሴፍም በግብፅ ምድር ልጆች ተወለዱለት፤ እነርሱም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ አስኔት የወለደችለት ምናሴና ኤፍሬም ናቸው። ሶርያዊት ዕቅብቱ የወለደችለት የምናሴም ልጅ ማኪር ነው። ማኪርም ገለዓድን ወለደ፤ የምናሴም ወንድም የኤፍሬም ልጆች ሱታላና ጠኀን ናቸው። የሱታላ ልጅም ኤዴን ነው።
የደቡብም ሰዎች የዔሳውን ተራራ፥ የቆላውም ሰዎች ፍልስጥኤማውያንን ይወርሳሉ፤ የኤፍሬምንም ተራራ፥ የሰማርያን፥ የብንያምንና የገለዓድን ሀገር ይወርሳሉ።
ውበቱ እንደ ላም በኵር ነው፤ ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፤ በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፤ የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።