Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 1:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ከዮሴፍ ልጆች፥ የኤፍሬም ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸውና በየአባቶቻቸው ቤቶች እንደየስማቸው ቊጥር ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ከዮሴፍ ልጆች፦ ከኤፍሬም ዝርያ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 “ከዮሴፍ ልጆች፥ የኤፍሬም ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለው፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 የም​ናሴ ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች- እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ከዮሴፍ ልጆች፥ የኤፍሬም ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 1:32
14 Referencias Cruzadas  

ደግሞም ሌላ ወንድ ልጅ ይጨመርልኝ” ስትል ስሙን ዮሴፍ ብላ ጠራችው።


የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ናቸው፤ እነርሱም ዮሴፍ በግብጽ ምድር ከኦን ከተማ ካህን ከጶጢፌራ ሴት ልጅ ከአስናት የወለዳቸው ናቸው።


ወንድሞቻችሁ የሆኑትን የእስራኤልን ሕዝብ እንዳሳደድኩ፥ እናንተንም ከፊቴ አሳድዳችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


“ከይሁዳ በስተደቡብ ያሉ ሕዝቦች የኤዶምን ምድር ይወርሳሉ፤ በምዕራብ ተራራዎች ግርጌ በሚገኘው ቆላማ ስፍራ የሚኖሩ ሕዝቦች የፍልስጥኤምን ምድር ይይዛሉ፤ የኤፍሬምንና የሰማርያንም ግዛት ይወስዳሉ፤ የብንያም ሰዎችም የገለዓድን ምድር ይወርሳሉ።


ከዛብሎን ነገድ የተቈጠሩት ኀምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።


ከኤፍሬም ነገድ የተቈጠሩት አርባ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ፤


ስለ ዮሴፍም ነገድ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ከላይ በሰማይ በሚዘንብ ዝናብ፥ ከታችም ከጥልቀት በሚገኘው ውሃ፥ ምድራቸውን ይባርክ።


የዮሴፍ ግርማ እንደ ኰርማ አስፈሪ ነው፤ ቀንዶቹም እንደ ጐሽ ቀንዶች ጠንካሮች ናቸው፤ በእነርሱም ሕዝቦችን ይወጋል፤ እስከ ምድር ዳርቻም ያባርራል፤ የኤፍሬም ዐሥር ሺሆች የምናሴም ሺሆች እንደዚያው ናቸው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos