የእስራኤልም ልጆች ከራምሴ ተነሥተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ከጓዝ ጋር ካሉት ሌላ ስድስት መቶ ሺህ ሰው የሚያህል እግረኛ ነበረ።
ዘኍል 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ ድምር፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ በየስማቸው ቍጥር፥ ወንዱን ሁሉ እያንዳንዱን ቍጠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የወንዶቹን ስም አንድ በአንድ በመዘርዘር መላውን የእስራኤል ማኅበረ ሰብ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው ቍጠሯቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እያንዳንዱን ወንድ አንድ በአንድ እንደየስማቸው ቍጥር የሕዝብ ቈጠራ አድርጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንተና አሮን፥ የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ በየነገዱና በየቤተሰቡ ኻያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነውን እያንዳንዱን ወንድ አንድ በአንድ እየቈጠራችሁ መዝግቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ ድምር፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ በየስማቸው ቍጥር፥ ወንዱን በየራሱ፥ ውሰዱ። |
የእስራኤልም ልጆች ከራምሴ ተነሥተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ከጓዝ ጋር ካሉት ሌላ ስድስት መቶ ሺህ ሰው የሚያህል እግረኛ ነበረ።
“አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር የወሰድህ እንደ ሆነ በቈጠርሃቸው ጊዜ መቅሠፍት እንዳይሆንባቸው፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ።
በማኅበሩም ከሚቈጠሩት የተገኘ ብር፥ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን፥ መቶ መክሊትና አንድ ሺህ ሰባት መቶ ከሰባ አምስት ሰቅል ነበረ።
እያንዳንዱም ሰው አንድ አንድ ዲድርክም አዋጣ፤ አንድ ዲድርክም እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን የሰቅል ግማሽ ነው፤ ይህም የተዋጣው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ከተቈጠሩ ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ሰዎች ነበረ።
በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበሩን ሁሉ ሰበሰቡአቸው፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ወንድ ሁሉ በየራሱ፥ በየወገኑም፥ በየአባቶቻቸውም ቤቶች፥ በየስማቸው ቍጥር ትውልዳቸውን ተናገሩ።
የስምዖን ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች የተቈጠሩ፥ እንደ እየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥