La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 9:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ​ዚ​ህም ሁሉ የታ​መ​ነ​ውን ቃል ኪዳን አድ​ር​ገን እን​ጽ​ፋ​ለን፤ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኖ​ቻ​ች​ንም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም ያት​ሙ​በ​ታል።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ከዚህ ሁሉ የተነሣም ጽሑፍ ላይ በማስፈር ግዴታ የምንገባበትን የውል ስምምነት እናደርጋለን፤ መሪዎቻችን፣ ሌዋውያናችንና ካህናታችንም ማኅተሞቻቸውን ያኖሩበታል።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እኛ የጽሑፍ ስምምነት ለማድረግ ወሰንን፤ በስምምነቱም ጽሑፍ ላይ መሪዎቻችን፥ ሌዋውያኖቻችንና ካህናቶቻችን ማኅተማቸውን አኖሩበት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህም ሁሉ የታመነውን ቃል ኪዳን አድርገን እንጽፋለን፥ አለቆቻችንም ሌዋውያኖቻችንም ካህናቶቻችንም ያትሙበታል።

Ver Capítulo



ነህምያ 9:38
10 Referencias Cruzadas  

ንጉ​ሡም በዓ​ምደ ወርቁ አጠ​ገብ ቆሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይከ​ተሉ ዘንድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንና ምስ​ክ​ሩ​ንም ሥር​ዐ​ቱ​ንም በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውና በፍ​ጹም ነፍ​ሳ​ቸው ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ በዚ​ህም መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን የቃል ኪዳን ቃል ያጸኑ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በቃል ኪዳን ጸኑ።


ካህኑ ኢዮ​አ​ዳም በእ​ር​ሱና በሕ​ዝቡ ሁሉ፥ በን​ጉ​ሡም መካ​ከል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ ቃል ኪዳን አደ​ረገ።


አሁ​ንም የቍ​ጣ​ውን መቅ​ሠ​ፍት ከእኛ እን​ዲ​መ​ልስ ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ቃል ኪዳን አደ​ርግ ዘንድ በልቤ አስ​ቤ​አ​ለሁ።


ንጉ​ሡም በዐ​ምዱ ቆሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ትሎ እን​ዲ​ሄድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንና ምስ​ክ​ሩን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም በፍ​ጹም ልቡና በፍ​ጹም ነፍሱ እን​ዲ​ጠ​ብቅ፥ በዚ​ህም መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን የቃል ኪዳን ቃል እን​ዲ​ያ​ደ​ርግ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን አደ​ረገ።


አሁ​ንም እንደ ጌታ​ዬና የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ትእ​ዛዝ እን​ደ​ሚ​ፈ​ሩት ምክር፥ ሴቶ​ችን ሁሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን እን​ሰ​ድድ ዘንድ ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ጋር ቃል ኪዳን እና​ድ​ርግ። ተነሥ እንደ አም​ላ​ካ​ች​ንም ትእ​ዛዝ ገሥ​ፃ​ቸው፤ እንደ ሕጉም ያድ​ርጉ፤


ያተ​ሙ​ትም እነ​ዚህ ናቸው፤ የሐ​ካ​ልያ ልጅ ሐቴ​ር​ሰታ ነህ​ምያ፥ ሴዴ​ቅ​ያስ፤


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተ​ሰ​ጠው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሁሉ፥ ፍር​ዱ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ ርግ​ማ​ን​ንና መሐ​ላን አደ​ረጉ።


ይህ፦ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ይላል፤ ያም በያ​ዕ​ቆብ ስም ይጠ​ራል፤ ይህም፦ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ብሎ በእጁ ይጽ​ፋል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ስም ይጠ​ራል።”


እነርሱም ሄደው ከጠባቆች ጋር ድንጋዩን አትመው መቃብሩን አስጠበቁ።