ነህምያ 9:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ግን ምሕረትህ ብዙ ነውና በምድረ በዳ አልተውሃቸውም፤ በመንገድም ይመራቸው ዘንድ የደመና ዓምድን በቀን፥ የሚሄዱበትንም መንገድ ያበራላቸው ዘንድ የእሳት ዓምድን በሌሊት ከእነርሱ አላራቅህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከርኅራኄህ ብዛት የተነሣ በምድረ በዳ አልተውሃቸውም፤ ቀን የደመናው ዐምድ በመንገዳቸው ላይ መምራቱን፣ ሌሊትም የእሳቱ ዐምድ በሚሄዱበት ላይ ማብራቱን አላቆመም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ግን ከርኅራኄህ ብዛት በምድረ በዳ አልተውካቸውም፤ በመንገድ እንዲመራቸው የደመና ዓምድ በቀን፥ የሚሄዱበትንም መንገድ እንዲያበራላቸው የእሳት ዓምድ በሌሊት ከእነርሱ አልተለየም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምሕረትህም ታላቅ በመሆኑ በዚያ ምድረ በዳ ይጠፉ ዘንድ አልተውካቸውም፤ ነገር ግን የደመናው ዐምድ በቀን ይመራቸው ነበር፤ የእሳቱ ዐምድ በሌሊት ያበራላቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ በምሕረትህ ብዛት በምድረ በዳ አልተውሃቸውም፥ በመንገድም ይመራቸው ዘንድ የደመና ዓምድ በቀን፥ የሚሄዱበትንም መንገድ ያበራላቸው ዝነድ የእሳት ዓምድ በሌሊት ከእነርሱ አልራቀም። |
ስለዚህ በሚያሠቃዩአቸው ሰዎች እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው፤ አስጨነቋቸውም፤ በመከራቸውም ጊዜ ወደ አንተ ጮኹ፤ ከሰማይም ሰማሃቸው፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት ታዳጊዎችን ሰጠሃቸው፤ ከሚያሠቃዩአቸውም እጅ አዳንሃቸው።
ያዕቆብ ሆይ፥ አንተም እስራኤል፥ አገልጋዬ ነህና ይህን ዐስብ፤ እኔ ፈጥሬሃለሁ፤ አንተም ባሪያዬ ነህ፤ እስራኤል ሆይ፥ አትርሳኝ።
የዚያች ምድር ሰዎች፥ አንተ እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብህ መካከል እንደ ሆንህ ሰምተዋል፤ አንተም፥ አቤቱ፥ ዐይን በዐይን እንደሚተያይ ተገልጠህላቸዋል። ደመናህም በላያቸው ቆመች። በቀንም በደመና ዐምድ ፥ በሌሊትም በእሳት ዐምድ በፊታቸው ትሄዳለህ።
አምላክህ እግዚአብሔር ይፈትንህ ዘንድ፥ በልብህም ያለውን ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያስጨንቅህ በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስብ።
እግዚአብሔር ለእርሱ ሕዝብ ያደርጋችሁ ዘንድ ተቀብሎአችኋልና፥ እግዚአብሔር ስለ ታላቅ ስሙ ሕዝቡን አይተውም።