La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 6:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔም እን​ዲህ ስል መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላክ​ሁ​ባ​ቸው፥ “እኔ ታላቅ ሥራ እሠ​ራ​ለሁ፤ እወ​ር​ድም ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም። ስለ​ምን ወደ እና​ንተ በመ​ም​ጣ​ቴና በመ​ው​ረዴ ሥራው ይታ​ጐ​ላል? ሥራ​ውን እንደ ፈጸ​ምሁ እመ​ጣ​ለሁ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔም፣ “ታላቅ ሥራ እየሠራሁ ስለ ሆነ፣ ወዳላችሁበት ስፍራ መውረድ አልችልም፤ ትቼው ወደ እናንተ ወርጄ ሥራው ለምን ይቆማል?” በማለት ይህን መልስ የሚያደርሱ መልእክተኞችን ወደ እነርሱ ላክሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔም እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁባቸው፦ “ትልቅ ሥራ እሠራለሁ፥ መውረድም አልችልም፤ ሥራውን ትቼ ወደ እናንተ በመውረዴ ሥራው ለምን ይቆማል?”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔም “አስቸኳይ ሥራ ስላለብኝ ተግባሬን አቁሜ እናንተ ወዳላችሁበት ስፍራ መውረድ አልችልም፤ ወደ እናንተ ለመምጣት ተብሎ ለምን ሥራው ይቆማል?” አልኳቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔም፦ ትልቅ ሥራ እሠራለሁ፥ እወርድም ዘንድ አይቻለኝም፥ ሥራውን ትቼ ወደ እናንተ በመውረዴ ስለ ምን ሥራው ይታጐላል? ብዬ መልእክተኞችን ላክሁባቸው።

Ver Capítulo



ነህምያ 6:3
9 Referencias Cruzadas  

ከቅ​ጥ​ሩም በስ​ተ​ኋላ በኩል ባለው በታ​ች​ኛው ክፍል በሰ​ዋራ ስፍራ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንና ጦራ​ቸ​ውን፥ ቀስ​ታ​ቸ​ው​ንም አስ​ይዤ ሕዝ​ቡን በየ​ወ​ገ​ና​ቸው አቆ​ም​ኋ​ቸው፤


ሰን​ባ​ላ​ጥና ጌሳም፥ “መጥ​ተህ በኦኖ ቈላ ውስጥ ባሉት መን​ደ​ሮች እን​ገ​ናኝ” ብለው ላኩ​ብኝ፤ ነገር ግን ክፉ ያደ​ር​ጉ​ብኝ ዘንድ ይመ​ክሩ ነበር።


እን​ዲ​ህም ቃል አራት ጊዜ ላኩ​ብኝ፤ እኔም እንደ ፊተ​ኛው ቃል መለ​ስ​ሁ​ላ​ቸው።


የዋህ ነገርን ሁሉ ያምናል፤ ዐዋቂ ግን ወደ ንስሓ ይመለሳል።


አንተ በም​ት​ሄ​ድ​በት በሲ​ኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕው​ቀ​ትና ጥበብ አይ​ገ​ኙ​ምና እጅህ ለማ​ድ​ረግ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ እንደ ኀይ​ልህ አድ​ርግ።


“እነሆ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


‘ይህ ሰው ሊሠራ ጀመረ፤ ግን መጨ​ረስ ተሳ​ነው’ እያሉ ሊዘ​ብ​ቱ​በት ይጀ​ም​ራሉ።


ነገር ግን ቀን ሳለ የላ​ከ​ኝን ሥራ ልሠራ ይገ​ባ​ኛል፤ ማንም ሥራ ሊሠራ የማ​ይ​ች​ል​ባት ሌሊት ትመ​ጣ​ለ​ችና።